Tender Detail

Tender Details

  • Company Agri Service Ethiopia (አግሪ ሰርቪስ ኢትዮጵያ)
  • Address ከግሎባል ሆቴል በስተጀርባ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0114-666417
  • Websitehttps://agriserviceethiopia.org/
  • Deadline18 Jul 2025, 12:00 AM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document Price500.00
  • Bid Security2.00
  • opening date2025-07-24 00:00:00
  • Categories

አግሪ ሰርቪስ ኢትዮጵያ የእርባታ ፍየሎች ግዥ በመፈጸም ለፕሮጄክቱ ተጠቃሚ አርብቶ አደሮች ለማሰራጨት አቅደዋል። በመሆኑም ብዛቱ 290 (ሁለት መቶ ዘጠና) የሆነ ጥራቱን የጠበቀ፣ አካባቢውን የተላመደ (የወይጦ ጉጂ ዝርያ) ቄብ የእርባታ ፍየሎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

Agri Service Ethiopia (አግሪ ሰርቪስ ኢትዮጵያ)


 

አግሪ ሰርቪስ ኢትዮጵያ

የእርባታ ፍየል ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ

 

አግሪ ሰርቪስ ኢትዮጵያ መንግስታዊ ያልሆነ የልማት ድርጅት ሲሆን በደቡብ ኢትዮጵያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ ከሜርሲ ሃንድስ ዩሮፕ (Mercy Hands Europe project) እና ብሬድ ፎር ዘወርልድ (Bread for the world) በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ የእርባታ ፍየሎች ግዥ በመፈጸም ለፕሮጄክቱ ተጠቃሚ አርብቶ አደሮች ለማሰራጨት አቅደዋል። በመሆኑም ብዛቱ 290 (ሁለት መቶ ዘጠና) የሆነ ጥራቱን የጠበቀ፣ አካባቢውን የተላመደ (የወይጦ ጉጂ ዝርያ) ቄብ የእርባታ ፍየሎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ተወዳዳሪዎች ማሟላት የሚጠበቅባቸው መስፈርቶች፡-

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ እና ንግድ ምዝገባ፣
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ እና የታክስ ከፋይ መለያ ሰርቲፊኬት፣
  3. የዘመኑን ግብር አጠናቆ ለመክፈሉ ማስረጃ፣
  4. በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚያስችል ጊዜው ያላለፈ ታክስ ክሊራንስ፣
  5. የጨረታ ማስከበሪያ 2% በባንክ በተረጋገጠ CPO ከጨረታው ሠነድ ጋር ማያያዝ
  6. የፍየልና የቁም እንስሳት አቅራቢነት ልምድ ያለው/ያላት
  7. የተጫራቹ ድርጅት አጭር ታሪክ /Company profile/፣
  8. አሸናፊ ከሆኑ ደቡብ ኢትዮጵያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ ፍየሎቹን በ30 ቀናት ማስረከብ፣ ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል አዲስ አበባ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ጎተራ ማሳለጫ ከፍ ብለዉ ግሎባል (ኢትዮጵያ) ሆቴል ጀርባ ከሚገኘው ከድርጅቱ ዋና ጽ/ቤት ወይም ዳሰነች ወረዳ ካሚገኘው የድርጅቱ ቅ/ጽ/ቤት ከሐምሌ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሐምሌ 11 ቀን 2017 ዓ.ም ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 9፡00 ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፣

ጨረታው ሐምሌ 11 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት በዋና መ/ቤት እና ዳሰነች ወረዳ የድርጅቱ ቅ/ጽ/ቤት ተዘግቶ ሐምሌ 17 ቀን 2017 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 በዋና መ/ቤት በጨረታው ላይ ለመገኘት ፍላጎት ባላቸው ተጫቾች/ህጋዊ ወኪል በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።

ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት ተከታታይ ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት ከታች በተገለፀው አድራሻ የሚወዳደሩበት የጨረታ ሰነድ ቴክኒካል እና ፋይናንስ እንዲሁም ኦሪጂናል እና ኮፒ በማለት ለይቶ በተለያየ ፖስታ በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

አሸናፊው ውል ከገባ በኋላ ምንም ዓይነት የዋጋ ጭማሪ አያደርግም።

መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ ከዚህ በታች በተገለፀው አድራሻ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

አግሪ ሰርቪስ ኢትዮጵያ

ግሎባል ሆቴል በስተጀርባ

አዲስ አበባ

ስልክ ቁጥር 0114-666417/0114-651212

ወይም

ዳሰነች ወረዳ የድርጅቱ ቅ/ጽ/ቤት

ስልክ ቁጥር 0911043366/0912210497/0940302730

 

Save Tender