Tender Detail

Tender Details

  • Company Love in Action Ethiopia (LIAE) (ላቭ ኢን አክሽን ኢትዮጲያ)
  • Address ሰሚት ከተባበሩት አደባባይ ወደ አቤም በሚወስደው መንገድ አሜሪካ ሜዲካል ሴንተር ገባ ብለው ባለው የግራው መንገድ ሰማያዊው የሰንሻይን አጥር እንደጨረሱ በስተግራ ባለው አስፓልት ስትታጠፉ በቀኝ በኩል ያለው ሶስተኛው ቤት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0910-49-12-33
  • Websitehttps://www.loveinactionethiopia.org/
  • Deadline10 Jul 2025, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-07-10 00:00:00
  • Categories Consultancy Service , Media

ላቭ ኢን አክሽን ኢትዮጵያ በአሁን ሰዓት ለሚተገብረው የቲ ቢ ፕሮጀክት ከዚህ በታች በተዘረዘሩት መስፈርቶች የሚዲያ አማካሪ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

Love in Action Ethiopia (LIAE) (ላቭ ኢን አክሽን ኢትዮጲያ)


 

ላቭ ኢን አክሽን ኢትዮጵያ

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

ድርጅታችን ላቭ ኢን አክሽን ኢትዮጵያ በጤና፤ በትምህርት፤ በኢኮኖሚ አቅም ግንባታ፤ በሰላም እና እርቅ ልማት፤ መልካም አስተዳደር እና በማህበራዊ ተጠያቂነት በማስፋት እና በማስረጽ፤ በድንገተኛ አደጋ ድጋፍ እና በመልሶ ማቋቋም፤ እና ሁለገብ የማህበረሰብ ድጋፍ ፕሮግራሞችን በመደገፍ ረገድ ከመንግስት እና ከተጠቃሚው ህብረተሰብ ጋር በመቀናጀት መጠነ ሰፊ ስራዎችን ላለፉት 23 አመታት በ10 ክልሎች በሚገኙ 497 ጣቢያዎች ሲሰራ መቆየቱ ይታወቃል። በመሆኑም በአሁን ሰዓት ለሚተገብረው የቲ ቢ ፕሮጀክት ከዚህ በታች በተዘረዘሩት መስፈርቶች የሚዲያ አማካሪ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

  • በቱሪዝም እና በጉዞ ጉዳዮች ላይ በሚዲያው ዘርፍ ላይ ከአምስት አመት በላይ መረጋገጥ የሚችል የስራ ልምድ ያለው
  • በቱሪዝም እና የጉዞ የቴሌቪዥን ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት ልምድ ያለው እና በራሱ አየር ሰዓት ወስዶ በቴሌቭዥን የሰራ ቢያንስ አምስት የጉዞ ፕሮግራሞችን ማቅረብ የሚችል
  • በማህበረሰብ ባህላዊ ስርዓት ጠንቅቆ የሚረዳ እና ለሚሰራው ፕሮግራም ሞያዊ ሀላፊነትን ወስዶ መስራት የሚችል
  • ከቲቢ በሽታ ጋር በተገናኘ የሚዲያ ስራዎችን ሰርቶ የሚያውቅ
  • ሙሉ የፕሮዳክሽን መሳሪያ ያለው እና በራሱ ፕሮግራሞችን ማዘጋጀት የሚችል
  • የሚዲያ ፕሮሞሽን ስራዎችን በመስራት ልምድ ያለው

ስለዚህ በዘርፉ የተሰማሩ የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የምስክር ወረቀት እና የታክስ መለያ (TIN) ማቅረብ የሚችሉ እንዲሳተፉ እየጋበዝን ዝርዝር የጨረታ መመሪያ እና ሰነድ ከቢሮ ይወስዳል። ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እ.አ.አ እስከ ጁላይ 8 2025 ባሉት ተከታታይ የስራ ቀኖች በስልክ ቁጥር +251-910-49-12-33, +251-926-35-36-51 ወይም fkyebeltal25@gmail.com ኢ-ሜል አድራሻ የጨረታ ሰነዱ በመጠየቅ መውሰድ የሚችሉ ሲሆን፤ አቅራቢዎች የዋጋ እና የቴክኒካል ፕሮፖዛል በዋና መ/ቤት እ.አ.አ እስከ ጁላይ 10 2025 እስከ 10፡00 ድረስ ማቅረብ ትችላላችሁ። ጨረታው እ.አ.አ ጁላይ 10, 10:30 በዋና መ/ቤት የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን።

ላቭ ኢን አክሽን ኢትዮጵያ ጨረታውን በከፊል እንዲሁም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- “ሰሚት ከተባበሩት አደባባይ ወደ አቤም በሚወስደው መንገድ አሜሪካ ሜዲካል ሴንተር ገባ ብለው ባለው የግራው መንገድ አዲስ አስፖልት ላይ የሰንሻይን አጥር እንደጨረሱ በስተግራ ባለው አስፖልት ስትታጠፉ በቀኝ በኩል ያለው ሶስተኛው ቤት

ለበለጠ መረጃ፡ በ +251-910-49-12-33 ወይም +251-926-35-36-51 መደወል ይችላሉ።

 

 

Save Tender