የትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅት ለህትመት ስራ አገልግሎት የሚውሉ Imported high quality White bond paper 80gsmx84cm እና የweboff set Yellow, Blue and Magenta Ink ለመግዛት ብቃት ያላቸው አስመጪ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
Educational Materials Production and Distribution Enterprise (የትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻ እና ማከፋፈያ ድርጅት)
የህትመት ግብዓት ግዥ የሃገር አቀፍ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- ት.መ.ማ.ማ.ድ/NCB/19/2017
የትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅት ለህትመት ስራ አገልግሎት የሚውሉ Imported high quality White bond paper 80gsmx84cm እና የweboff set Yellow, Blue and Magenta Ink ለመግዛት ብቃት ያላቸው አስመጪ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ነጥቦች ግንዛቤ ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
- በዘርፉ ተዛማጅነት ያለው የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፤ የታክስ ክሊራንስ ደብዳቤ፤ የተ.እ.ታ ምዝገባ ሰርተፊኬት፤ ግብር ከፋይ ሰርተፊኬት እና የአቅራቢ ምዝገባ ሰርተፊኬት እና ናሙና ማቅረብ የሚችሉ መሆኑ አለባቸው።
- ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልጸውን ሰነድ የማይመለስ ብር 600 /ስድስት መቶ ብር/ በመክፈል ከትም/መሳሪ/ማም/ማከ/ድርጅት ዘወትር በሥራ ሰዓት ጠዋት ከ2፡00 ሰዓት እስከ 6፡30 ሰዓት እንዲሁም ከ7፡30 ሰዓት እስከ 10፡30 ሰዓት ከቢሮ ቁጥር 35 መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና White bond paper 80gsmx84cm እና የWeboff set Ink 300,000.00 (ሶስት መቶ ሺህ ብር) በሲፒኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ጨረታው ሃምሌ 15 ቀን 2017 ዓ.ም በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ በዚሁ እለት በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ይከፈታል።
- ከላይ የተዘረዘሩትንና በጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተመለከቱትን ግዴታዎች የምታሟሉ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ ትችላላችሁ።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ Tel፡- 011-646-3481 መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
የትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻ እና ማከፋፈያ ድርጅት
