አቃ/ቃ/ክ/ከ/ፖሊስ መምሪያ በ2017 በጀት አመት ለአመራርና አባል የሚጠቀሙበት የዳቦ ዱቄት፣ ዘይት፣የዳቦ፣ ማሻሻያ፣ እርሾ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር አቃ/ቃ/ክ/ከ/ፖ/መምሪያ 003 ቀን 09/10/2017 ዓ/ም
አቃ/ቃ/ክ/ከ/ፖሊስ መምሪያ በ2017 በጀት አመት ለአመራርና አባል የሚጠቀሙበት የዳቦ ዱቄት፣ ዘይት፣ የዳቦ፣ ማሻሻያ፣ እርሾ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት የሚፈልግ ሲሆን፡-
|
ሎት |
የጨረታ አይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ መጠን |
|
01 |
አንደኛ ደረጃ የዳቦ ዱቄት |
የጠቅላላዉ እቃ ዋጋ 2% |
|
02 |
ባለ 20 ሊትር የምግብ ዘይት |
>> >> >> |
|
03 |
ባለ 500 ግራም የዳቦ ማሻሻያ |
>> >> >> |
|
04 |
ባለ 500 ግራም የዳቦ እርሾ |
>> >> >> |
ስለዚህ፡- ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟሳት አለባቸው
- በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆነ እና በዘርፉ የተሰማሩ ለመሆናቸው በጀርባው ይመልከቱ የሚል ፅሁፍ በግልፅ ማቅረብ አለባቸው።
- የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ፡፡
- ተጨማሪ አሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
- የታደሰ የዘመኑን ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- የታደሠ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው።
- የመንግስት መ/ቤቶች ለሚያመጡት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የአቀራቢዎች የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው።
- በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከሊራንስ ማቅረብ አለበት፤
- አማራጭ ዋጋ ሆነ አማራጭ እቃ በዚህ ጨረታ ማቅረብ አይቻልም።
- በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ የጨረታ ውጤት እንደታወቀ ተመላሽ የሚሆን በሎቱ ለፊት የተቀመጠውን የገንዘብ መጠን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና አቃ/ቃ/ክ/ከ/ፖሊስ መምሪያ ተብሎ በተዘጋጀ ከባንክ በተመሰከረበት ቼክ ወይም ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ቴከኒካል ሰነዶችንና የዋጋ ማቅረቢያዎችን/ፋይናንሻል/ሰነዶች በተለያየ ፖስታ ታሽጎ ለየብቻ መቅረብ አለባቸው ማንኛውንም ተጫራቾች የሚያስገባው ሰነድ ፋይናንሻል የጨረታ ሰነድ አንድ ኦሪጅናል አንድ ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማሸግ በፖስታው ላይ የጨረታ ሰነዱን ቁጥር በትክክል መፃፍ እንዲሁም በፖስታው ላይ ማህተም በመምታት ማስገባት ያለበት ሲሆን፣ ስርዝ ድልዝ በፍሉድ የጠፋ ሰነድ ዋጋ ያልተሞላበት ዝርዝር ተቀባይነት የሌለው መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚያሲዙት ሲ.ፒ.ኦ. ከቴክኒከ ሰነዶች ጋር በአንድ ላይ ታሽገው መቅረብ አለባቸው።
- በጨረታ አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች ዕቃውን በራሳቸው ትራንስፖርት አቃ/ቃ/ክ/ከ/ፖሊስ መምሪያ በፍላጎት መገለጫው በተጠቀሰው መሰረት ጥራታቸው ተረጋግጦ የማስረከቢያ ቦታ ድረስ በማምጣት ማስረከብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ቃሊቲ ከራውን ሆቴል አጠገብ የተባበሩት ማደያ ፊት ለፊት በሚገኘው በአቃ/ቃ/ክ/ከ/ፖሊስ መምሪያ 3ኛ ፎቅ 303 ቁጥር ገዢ እና ፋይናንስ ቢሮ ቀርበው በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 150.00 /አንድ መቶ ሀምሳ ብር/ በመከፈል መግዛት ይችላሉ፣
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 06 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30 ስስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ እንዲሁም በማግስቱ በ7ኛው ቀን እስከ ጠዋቱ 3፡00 ሠዓት ድረስ ጨረታው ክፍት ሆኖ ስለሚቆይ አቃ/ቃ/ክ/ከ/ፖሊስ መምሪያ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- በ7ኛው ቀን ጠዋት 3:00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ 4፡00 ሰዓት ሲሆን በመ/ቤቱ ስብሰባ አዳራሽ ዉስጥ ይከፈታል፣
- የጨረታው መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሱ ባለው መደበኛ የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው 3፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡00 ሲሆን ይከፈታል፡፡
- ዘግይተው የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተወዳዳሪዎች የሚወዳደሩባቸዉን ዕቃዎች ሳምፕል ከጨረታዉ መከፈት ቀን በፊት መቅረብ አለባቸዉ። ሳምፕል ያላቀረበ ከጨረታዉ ዉድቅ ይሆናል።
ለበለጠ መረጃ
በስ/ቁጥር 011 439 3196 / 011 471 7484
አቃ/ቃ/ክ/ከ/ፖሊስ መምሪያ የዕቃዉ ልዩ ሁኔታዎች ተያይዘዋል እነዚህም ማንኛዉንም የዉል ውጤት ለመመስረት አይነተኛ ክፍል ናቸዉ
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ
