የአምቦ የነ/ህ/ሥራ ዩኒየን ከአባላቱ ገዝቶ በአምቦ እና በቡራዩ ታጠቅ ማዕከላዊ መጋዘን ያከማቸውን በቆሎ ብዛቱ 10000 (+or-) ኩንታል የአንዱ ኩንታል የጨረታ መነሻ ዋጋ በብር 3400 ነጭ ገብስ ብዛቱ 400 ኩንታል የአንዱ ኩንታል መነሻ ዋጋ በ9000 ብር አወዳድረው መሸጥ ይፈልጋል፡፡
አምቦ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒየን
የእህል ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የአምቦ የነ/ህ/ሥራ ዩኒየን ከአባላቱ ገዝቶ በአምቦ እና በቡራዩ ታጠቅ ማዕከላዊ መጋዘን ያከማቸውን በቆሎ ብዛቱ 10000 (+or-) ኩንታል የአንዱ ኩንታል የጨረታ መነሻ ዋጋ በብር 3400 ነጭ ገብስ ብዛቱ 400 ኩንታል የአንዱ ኩንታል መነሻ ዋጋ በ9000 ብር አወዳድረው መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ተጫራቾቹ ማሟላት ያለባቸው ነገሮች
- ተጫራቾች የጨረታ ሰንድ ከዩኒያኑ ጋብያ ክፍል በ 500 ብር መግዛት ይችላሉ
- የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን መረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾቹ የበቆሎውን ሁኔታ በአምቦ እና በቡራዩ ታጠቅ በዩኒያኑ መጋዘን ገብሱን አምቦ ባለው የዩኒየኑ መጋዘን በስራ ሰዓት ተገኝተው ማየት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ /CPO/ በቅድሚያ 5% ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው እንዳበቃ ለተሸናፊዎች ሲመለስላቸው አሸናፊዎች ከግዥ ውስጥ የሚታሰብላቸው ይሆናል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዘጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታተይ ቀናት አየር ላይ ከቆየ በኋላ በ22ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት ጠዋት ታሽጎ በዛው ቀን ጠዋት በ5፡00 ሰዓት ላይ አምቦ ባለው በዩኒየኑ ቢሮ ይከፈታል፡፡ 22ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል።
- ተጫራቾች ተወካዮቻቸው በጨረታው መክፈቻ ላይ ለመገኘት ከድርጅታቸው የውክልና ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ተወዳዳሪዎች በሙሉ ባይገኙም በተገኙ ተጫራቾች ፊት ጨረታው በዕለቱ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የመግዣ ዋጋቸውንና ለጨረታው የተጠየቁትን መረጃዎች በፖስታ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ በገባው ውል መሰረት ክፍያ አጠናቆ ካሸነፉበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ ማንሳት ይኖርበታል፡፡ አሸናፊው በተሰጠው ቀናት ውስጥ ያላነሳ እንደሆነ ያስያዘው ገንዘብ የማይመለስለት ከመሆኑም በላይ በየቀኑ ለእያንዳንዱ ኩንታል የመጋዘን ኪራይ ብር 0.5 ይከፍላል፡፡
- አንድ ተጫራች በሌላው ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችልም፡፡
- ጨረታውን ያሸናፈ አሸናፊ ለውል ማስከባሪያ ጠቅላለውን ዋጋ 10% የባንክ ጋራንት ማስያዝ ይኖርበታል።
- ዩኒየኑ በበቆሎው ሽያጭ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው አምቦ የገ/ህ/ሥራ ዩኒየን
ለበለጠ መረጃ ስልክ 0913379435: 0112363399 ይጠቀሙ፤
የአምቦ የገ/ህ/ሥራ ዩኒየን
