Tender Detail

Tender Details

  • Company በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ
  • Address ሠመራ ፡ አፋር ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 033-366-60-22
  • Website
  • Deadline16 Jun 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-06-16 00:00:00
  • Categories Agriculture And Farming , Building Construction

የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የእርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት በአብኣላ ወረዳ የሀራ መሊ ቀበሌ የሸጎሎሌ የመስኖ ካናል ግንባታ ስራ ለመፈጸም በአገር ውስጥ ገበያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ስራውን ማሰራት ይፈልጋል፡፡

በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የእርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት በአብኣላ ወረዳ የሀራ መሊ ቀበሌ የሸጎሎሌ የመስኖ ካናል ግንባታ ስራ ለመፈጸም በአገር ውስጥ ገበያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ስራውን ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራች ከዚህ በታች የተገለጹትን ነጥቦች ማሟላት ይኖርባቸዋል።

  1. ተጫራቾች ግዴታ ማሟላት ያለባቸው የቅድሚያ መወዳደሪያ መስፈርቶች ማለትም፡-
    1. በዘርፉ የዘመኑ የታደሠ ንግድ ፈቃድ
    2. የንግድ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ያለው
    3. ንግድ ፈቃድ ምዝገባ ሰርተፊኬት ያለው
    4. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ
    5. ሲ.ፒ.ኦ
    6. የጨረታ ሰነድ ግዥ የፈጸመ እና
    7. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያለው ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታውን ሰነድ ከአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የእርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ በግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/የዳይሬክቶሬት ክፍል ብር 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች በእያንዳንዱ በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነዶች ላይ ተጫራቾች ወይም የህጋዊ ወኪል ፈርማና ማህተም ማድረግ ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና /Bid Bond/ ለውድድር የሚያቀርቡት ከጠቅላላ ዋጋ 1% በሲ.ፒ.አ (C.P.O) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ተወዳዳሪዎች በውድድሩ ከተሸነፈ ለዋስትና ያስያዙት የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና የጨረታው ውጤት ታውቆ ውል ከተፈራረሙ በኋላ ወዲያውኑ የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና ያስያዙት የውል ማስከበሪያ ይመለስላቸዋል።
  5. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርቡትን የውድድር ጥያቄም ሆነ ሰነድ በመ/ቤቱ በኩል ተቀባይነት አይኖረውም።
  6. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 10 ቀናት የሚቆይ ሆኖ በ11ኛው የስራ ቀን ጧት 4፡00 ሰአት የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋ ሲሆን በእለቱ ጧት 4፡30 ሠአት በአፋር ብሄራዊ ክ/መ/ የእርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ አዳራሽ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  7. ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  8. ለተጨማሪ መረጃ በቢሮው ስልከ ቁጥር 033-366-60-22 ወይም 033-366-33-76 ደውለው ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

 

በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የእርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ /ሠመራ/

 

Save Tender