Tender Detail

Tender Details

  • Company በልደታ ክ/ከተማ ት/ጽ/ቤት ልደታ ልማት የመጀ/መካ/ደ/ት/ቤት
  • Address ልደታ ክ/ከተማ በወረዳ 09 ስር የሚገኘው ልደታ ልማት የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0115577520
  • Website
  • Deadline04 Jun 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-06-05 00:00:00
  • Categories Food And Beverage , Supply Of Animals

በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 9 አስተዳደር ስር ያለው ልደታ ልማት የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የ2017 ዓ.ም በጀት አመት የሚያስፈልገውን የከተማ የግብርና ግብዓቶች (የአሳ እና የዶሮ) በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በልደታ ክ/ከተማ ት/ጽ/ቤት ልደታ ልማት የመጀ/መካ/ደ/ት/ቤት


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥው መለያ ቁጥር 02/2017 ዓ.ም

 

በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 9 አስተዳደር ስር ያለው ልደታ ልማት የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የ2017 ዓ.ም በጀት አመት የሚያስፈልገውን

ሎት1. የከተማ የግብርና ግብዓቶች (የአሳ እና የዶሮ) የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 5000.00 በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ በመንግስት ግ/ን/አስ/ኤጀንሲ ድረ -ገጽ ላይ በአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር የተመዘገቡ የቲንና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤

  1. ተጫራቾች ጨረታውን በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /ሲፒኦ/ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  2. ተጫራቾች ጨረታቸውን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ በተከታታይ 10 የስራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) በመክፈል በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ልደታ ልማት የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ10ኛው (አስረኛው) ቀን በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በማግስቱ 3፡00 ሰዓት በልደታ ልማት የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ/ት/ቤት ይከፈታል።
  5. የመክፈቻው ቀን ቅዳሜ ፤ እሁድ ወይም በበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ የስራ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው ሎት 1 በቀረበው የፍላጎት መግለጫ መሰረት የተሟላ የፍላጎት መግለጫ ማዘጋጀትና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል ፡፡
  7. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች የሞሉት ዋጋ ከቫት ጋር መሆኑን መለየት አለባቸው፡፡
  8. የዘገየ ጨረታና ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
  9. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸው እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈጻሚው መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ (ጥያቄ)፡- አድራሻ ልደታ ክ/ከተማ በወረዳ 09 ስር የሚገኘው ልደታ ልማት የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት

ስልክ ቁጥር፡- 0115577520/0115578474

 

በልደታ ክ/ከተማ ት/ጽ/ቤት ልደታ ልማት የመጀ/መካ/ደ/ት/ቤት

 

Save Tender