የአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በ2018 የበጀት ዓመት የጥበቃ ስራ ፤ የፅዳት ስራ እና የግቢ ውስጥ እና ለአካባቢ አረንጓዴ ልማት እንክብካቤ outsource በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Adama Hospital Medical College (የአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በ2018 የበጀት ዓመት የጥበቃ ስራ ፤ የፅዳት ስራ እና የግቢ ውስጥ እና ለአካባቢ አረንጓዴ ልማት እንክብካቤ outsource በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፤ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መስፈርቶች የምታሟሉ ነጋዴዎች መወዳደር ትቸላላችሁ።
- 2017 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ በዘርፉ ያላችሁ እንዲሁም የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ።
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ ስለመሆን መረጃ ማቅረብ የሚችል
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ፅ/ቤት በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- ለፅዳት ስራ ከአዳማ ከተማ የምግብ ዋስትና እና የስራ ፈጠራ ክህሎት/ ከጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ቢሮ የድጋፍ ደብዳቤ ማምጣት የሚችል እና በፅዳት ስራ ላይ በ”IMX” የተደራጁ መሆን አለባቸው።
- ለጥበቃ ስራ ከሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የድጋፍ ደብዳቤ ማምጣት የሚችል፣
- ከዚህ በፊት ከአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በስነ-ምግባርም ሆነ በሌላ ምክንያት ደብዳቤ የተፃፈበት መወደዳር አይችልም።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የጨረታ ስነድ ኮፒና ኦሪጅናል ለየብቻ በተለያየ ፖስታ ማሸግ አለባቸው።
- ስርዝ ድልዝ ያለው፣ የማይታይ የጨረታ ሰነድ ወይም የዋጋ ዝርዝር ተቀባይነት የለውም።
- ጨረታውን ካሸነፋ በኋላ የውል ማስከበሪያ የአሸነፉበትን ዋጋ 10% ማስያዝ የሚችል፣
- ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምር ከኮሌጁ ግዥና ፋይናንስ የስራ ሂደት ክፍል ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ለእያንዳንዱ 200 /ሁለት መቶ ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ አለባቸው።
- የፅዳት ስራ ጨረታው የሚከፈተው በ05/10/2017 ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- የጥበቃ ስራ ጨረታው የሚከፈተው በ05/10/2017 ከቀኑ 9፡30 ሰዓት ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- የግቢ ውስጥ እና አካባቢ አረንጓዴ ልማት እንክብካቤ ስራ ጨረታው የሚከፈተው 06/10/2017 ከቀኑ 9:30 ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራቾች የሚሞሉትን ዋጋ በመስሪያ ቤቱ ሰነድ ብቻ ላይ መሆን አለበት።
- የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ 10,000 (አስር ሺ) ብር በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ በ "CBE, CBO, በ"Singe" ባንክ ብቻ ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0228123956 ደውለው መረዳት ይችላሉ።
የአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ
