የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን አንፀባራቂ ጃኬት በድጋሚ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎችን በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
Addis Ababa Water and Sewerage Authority (የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር REBID/NCB/GOV/AAWSA/G004/2016
የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን አንፀባራቂ ጃኬት በድጋሚ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎችን በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
- ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት መገናኛ ከሚገኘው ዋና መ/ቤት ምድር ቢሮ ቁጥር 13 በመገኘት ከላይ ለተጠቀሰው ግዥ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 600 (ስድስት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በመንግስት የግዥና የንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ በዘርፉ በዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ በድረ-ገፅ የተመዘገበ፤ ለዘመኑ ሕጋዊ እና የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ የምስክር ወረቀት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ እና ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ በመወዳደሪያ ኤንቨሎፑ ውስጥ በማድረግ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ጨረታውን ለመሳተፍ ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ቢያንስ ለ90 ቀናት ጸንቶ በCPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ይህንኑም እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ከዋናው ቴክኒክ ሠነድ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለበት፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሣባቸውን በሁለት ፖስታ /Two envelope/ ቴክኒክና ፋይናንሺያል ዋናና ቅጅ በማለት ለእያንዳንዱ ምድብ ለየብቻ ማቅረብ አለባቸው።
- አሸናፊው ተጫራች ላሸነፈባቸው የእቃ ዝርዝር ዋጋ መጠን 10% ከውል በኋላ ማስያዝ ይኖርበታል።
- የተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሠነድ ለ60 /ስልሣ/ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን አለበት፡፡ ከዚህ ያነሰ የጨረታ ዋጋ ፀንቶ መቆያ ጊዜ ያቀረበ ተጫራች ከጨረታው ይሰረዛል፡፡
- የጨረታ ሠነዱን በስሙ አስመዝግቦ ያልገዛ ማንኛውም ተወዳዳሪ በጨረታው መሳተፍ አይችልም።
- ጨረታው ግንቦት 18 ቀን 2017 ዓ.ም. ከሰዓት በኋላ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዕለቱ በ8፡30 ሰዓት 4ኛ ፎቅ በመ/ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ከጨረታው መዝጊያ ሰዓትና ቀን ዘግይቶ የሚመጣ ማንኛውም የመወዳዳሪያ ሠነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- የሚቀርበው ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስን ያካተተ መሆን አለመሆኑን በግልጽ ተለይቶ መቀመጥ አለበት። ይህንን ያልገለፀ ተወዳዳሪ ያቀረበው ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስን እንዳካተተ ተደርጐ ይቆጠራል፡፡
- ገዥው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተጠቀሱትን ዕቃዎች በ20% የመጨመር ወይም በ20% የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የባለስልጣን መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡ መገናኛ ከገቢዎች ሚኒስቴር አጠገብ ያለው ሰማያዊ ህንጻ ምድር ቢሮ ቁጥር 113
ስልክ :- 011 663 08 57/011 662 00 10
የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን
