Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)
  • Address ቦሌ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251115174918
  • Websitehttps://corporate.ethiopianairlines.com/
  • Deadline30 May 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-05-30 00:00:00
  • Categories Agricultural , Food Items And Drinks

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለሠራተኞች ካፍቴሪያ አገልግሎት የሚውሉ ባለ500 ሚሊ ሊትር የፕላስቲክ ከረጢት ወተት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የጨረታ ቁጥር፡ -SSNT-T538

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለሠራተኞች ካፍቴሪያ አገልግሎት የሚውሉ ባለ500 ሚሊ ሊትር የፕላስቲክ ከረጢት ወተት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ የወተት አምራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ።

  1. በአገልግሎቱ ዘርፍ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው ፤ ለ2017 የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ እና የTIN ምዝገባ ወረቀት ያለው፣ VAT ተመዝጋቢ የሆነ ፣ አንድ (1) ዓመትና እና ከዛ በላይ የሰራ
  2. ከኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሲቲትዩት እና ከኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ አንድ መቶ ብር (ብር 100.00) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T538 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ቅጂውን (scan copy) በማድረግ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ።
  4. በጨረታው የሚካፈል ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርቡትን ዋጋ ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርበታል። ከማንኛውም ኢንሹራንስ የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም።
  5. ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን (ቴክኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል እስከ ግንቦት 22 ቀን 2017 ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ አየር ማረፊያ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መስሪያ ቤት በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 9:00 ሰዓት ይከፈታል።

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡-

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ

ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ዋና መስሪያ ቤት

ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል

ስልክ ቁጥር፡ +251-115-17-49-18

አሰፋ ይሉ

ኢ-ሜይል፡AssefaH@ethiopianairlines.com

 

አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

Save Tender