የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግስት ፋይናንስ ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት በክልሉ ውስጥ ለሚገኙ ለክልል ተቋማት ዞኖችና ወረዳዎች ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎችን በማዕቀፍ ግዥ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ቁጥር የጋራ ግዥና ንብረት ማስወገደ 03/2017
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግስት ፋይናንስ ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት በክልሉ ውስጥ ለሚገኙ ለክልል ተቋማት ዞኖችና ወረዳዎች ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎችን በማዕቀፍ ግዥ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
- በመስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የሚያሳይ ሰነድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ፣ ግብር የተከፈለበት ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 700 /ሰባት መቶ ብር/ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ፋይናንስ ቢሮ የግዥ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተው አካውንት ቁጥር 1000454348471 ገቢ በማድረግ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ /CPO/ በኢትዮጵያ ብር 500,000 /አምስት መቶ ሺህ/ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፋይናንስ ቢሮ ስም በማሰራት ከጨረታው ሰነድ ጋር በማዘጋጀት አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በመሙላት በሰም በመሙጫ በታሸገ አንድ ኤንቨሎፕ ኦሪጅናልና ኮፒ በማዘጋጀት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ ቀናት ባሉ የስራ ቀናት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ፋይናንስ ቢሮ የጋራ ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ዘርፍ በመቅረብ ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- የጨረታው ሳጥን በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት ከቀኑ 8:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፋይናንስ ቢሮ የጋራ ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ዘርፍ ቢሮ ላይ ይከፈታል። 16ኛው ቀን የመንግስት የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል።
- ሆኖም የተጫራቾች ወይም የህጋዊ ወኪሎች ያለመገኘት የጨረታ መከፈት ሂደት አያስተጓጉልም የጨረታው አሸናፊ ማሸነፉ ከተገለጸበት ጀምሮ ባሉት 5 የስራ ቀናት በኋላ ቀርቦ ውል መግባት የሚጠበቅበት ሲሆን የውል ማስከበሪያ የውሉን 10% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /C.P.O/ ማስያዝ ይጠበቅበታል።
- መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር- 0473312555
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝ/ክል/ፋይናንስ ቢሮ ቦንጋ
