Tender Detail

Tender Details


የገላን ጉራ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2017 ዓ.ም አገልግሎት ላይ የሚውሉ የተለያዩ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

የገላን ጉራ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡-001/2017

 

የገላን ጉራ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2017 ዓ.ም አገልግሎት ላይ የሚውሉ የተለያዩ እቃዎች

ማለትም፡-

  • የደንብ ልብስ
  • አላቂ የቢሮ እቃዎች
  • አላቂ የትምህርት እቃዎች
  • አላቂ የፅዳት እቃዎች
  • ልዩ ልዩ መሳሪያዎች
  • ቋሚ እቃዎች

በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በዚህ መሰረት ተጫራቾች

  1. በመንግስት እቃ አቅራቢነት ተመዝግበው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እና ቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች በዘርፉ ወይም በመስኩ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆን አለባቸው።
  3. የዘመኑ ግብር የከፈሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች ተጨማሪ እሴትታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
  5. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በት/ቤቱ ፋይናንስ ከፍል ብር 400 /አራት መቶ/ ብር በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ በግልፅ በመሙላት በመጨረሻ ቦታ ላይ ስም ፤ ፊርማና ህጋዊ ማህተም በማኖር በታሸገ ኢንቨሎፕ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን በማሸግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ከ2፡00-11፡00 ዋጋቸውን በመሙላት በተጠቀሰው የሥራ ሰዓት የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  7. ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሲፒዮ ብር 2 /ሁለት ፐርሰንት/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  8. ተጫራቾች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ጨረታው ሊዘጋ አንድ ቀን እስኪቀረው ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታውን አሸናፊ ሆነው ከተገኙ በኋላ 10% ባሸነፉበት እቃ መጠን መሰረት የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርቦታል፡፡
  10. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክር ከጨረታው ውጪ እንደሚሆንና የጨረታውን ማስከበሪያ CPO እንደሚወረስባቸው ማወቅ አለባቸው።
  11. ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በተዘጋ በቀጣዩ የሥራ ቀን በ5፡00 ሰዓት በት/ቤቱ የግ/ፋይ/ንብ/አስተዳደር ቢሮ ይከፈታል፡፡
  12. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0925275083

 

አድራሻ፡- በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ገላን ጉራ አዲሱ ካሳንቺስ ሰፈር

 

የገላን ጉራ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት

 

Save Tender