Tender Detail

Tender Details

  • Company Amhara Industry Parks Development Corporation (የአማራ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን)
  • Address ደ/ብርሃን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት : አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-637-62-89
  • Websitehttps:// amharaipdc.gov.et
  • Deadline09 May 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-05-09 00:00:00
  • Categories Building Construction , Ceramic Product And Ceramic Work

የአማራ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ደ/ብርሃን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በደ/ብርሃን ከተማ አጼ ዘርዓያዕቆብ ከፍለ ከተማ ኃ/ማርያም ማሞ ቀበሌ የሚገኘውን የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ክላስተር ማዕከል ባለ 4 ወለል ህንጻ ሼድ የአሸንዳና የጎረንዳዮ ጥገና ስራ እና የቢሮ 2 /ሁለት/ ክፍሎች የጂብሰምና የወለል ሴራሚክ ስራ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

Amhara Industry Parks Development Corporation (የአማራ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን)


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የአማራ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ደ/ብርሃን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በደ/ብርሃን ከተማ አጼ ዘርዓያዕቆብ ከፍለ ከተማ ኃ/ማርያም ማሞ ቀበሌ የሚገኘውን የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ክላስተር ማዕከል ባለ 4 ወለል ህንጻ ሼድ የአሸንዳና የጎረንዳዮ ጥገና ስራ እና የቢሮ 2 /ሁለት/ ክፍሎች የጂብሰምና የወለል ሴራሚክ ስራ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

በጥገና ስራው መሳተፍ የሚችሉ ተጫራቾች ሊያሟሉ የሚገባቸው መስፈርቶች፡-

  1. ደረጃ 8 GC/BC እና በላይ የሆነ ማንኛውም ተቋራጭ፣
  2. ህጋዊ በዘመኑ በ2017 ዓ.ም የታደሰ የንግድ የስራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN number/፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ መሆኑን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
  3. በ2017 ዓ.ም የስራ ዘመን የታደሰ መሆኑን የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል & ሆኖ በክልል ንግድ ፈቃድ ያወጡ ከክልል ከተማ መሰረተ ልማት ቢሮ ወይም የዞን መምሪያ፣ ከፌዴራል ንግድ ፈቃድ ያወጡ ከፌዴራል ከተማና መሰረተ ልማት ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ያወጡ፣
  4. ተጫራቾች ለስራው የሚያስፈልገውን ማቴሪያል እና የሰው ኃይል ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከደ/ብርሃን ከተማ አማራ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ደ/ብርሃን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ግዥ/ፋ/ጠ/አገ/ቡድን ቢሮ ቁጥር-03 የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመግዛት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ20 /ሃያ/ ተከታታይ ቀናት ሆኖ ቅዳሜ ግማሽ ቀን እስከ 6:30 ድረስ የስራ ቀን መሆኑ ታሳቢ ተደርጎ የጨረታ ሰነዱን በመሙላት የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ 2% የማያንስ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም ሲፒኦ በአማራ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ደብረብርሃን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስም ተሰርቶ የሚቀርብ ሲሆን ከጨረታ ሰነዱ ጋር በታሸገ ኤንቨሎፕ ዋና እና ኮፒ በአብክመ ኢፓልኮ ደ/ብርሃን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ግዥ/ፋ/ጠ/አገ/ቡድን ቢሮ ቁጥር-03 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  6. ጨረታው በ21ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ላይ በአማራ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ደ/ብርሃን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ግዥ/ፋ/ጠ/አገ/በድን ቢሮ ቁጥር-03 ይከፈታል፡፡ ሆኖም የጨረታ መክፈቻው ቀን የበዓል ቀን ላይ ካረፈ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተቀመጠው መስፈርትና የስራ ዝርዝር መሰረት ዋጋ መሙላት የሚኖርበት ሲሆን በተቀመጠው የስራ ዝርዝር መሰረት ዋጋ ያለመሙላት፣ በራስ የዋጋ መሙያ ቅጽ ሞልቶ ማቅረብ፣ ስርዝ ድልዝ መኖር አንዱ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  8. አሸናፊው ከተገለጸ በኋላ አሸናፊው ተጫራች የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋው 25% የማያንስ በአማራ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ደብረብርሃን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስም ተሰርቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  9. አሸናፊው ከተገለፀ በኋላ ካሉት 5 ተከታታይ ቀናት በኋላ ባሉት በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ቀርቦ የውል ማስከበሪያ ካላስያዘ እና ውለታ ካልፈፀመ አሸናፊነቱ ተሰርዞ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ለኮርፖሬሽኑ ገቢ ይሆናል፡፡
  10. ጽ/ቤቱ ጥገና የሚከናወንበትን ሳይት ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን በኋላ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00-9፡00 ስለሚያስጎበኝ ማየት የምትፈልጉ ተገኝታችሁ ማየት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  11. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

 

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-637-62-89/ 011-637-58-41 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

የአማራ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ደ/ብርሃን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

 

Save Tender