ግዥ ፈፃሚ መ/ቤት በደቡብ ኢት/ያ ህ/ክ/መንግስት በወላይታ ዞን የአበላ አባያ ወረዳ ፋይ/ጽ/ቤት ለወረዳው ግብርና ጽ/ቤት በሴፍትነት ፕሮግራም -5 ካፒታል በጀት በሎት 1/የኩሬ ቁፋሮ ዙሪያ አጥርን ጨምሮ ሎት 2/ የንብ ማነብያ ዘመናዊ የንብ ቀፎ በዚሁ መሠረት በሎት 1 የኩሬ ቁፋሮ 10,000 ሜትር ክዩብ ሎት 2 የንብ ማነብያ ዘመናዊ የንብ ቀፎ የግልጽ ጨረታ ዘዴን በመጠቀም አወዳድሮ ለማሰራት እና ለመግዛት ይፈልጋል ::
በደቡብ ኢትዮጵያ ክ/በወላይታ ዞን የአበላ አባያ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
2ኛ ዙር የወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/2017
ግዥ ፈፃሚ መ/ቤት በደቡብ ኢት/ያ ህ/ክ/መንግስት በወላይታ ዞን የአበላ አባያ ወረዳ ፋይ/ጽ/ቤት ለወረዳው ግብርና ጽ/ቤት በሴፍትነት ፕሮግራም -5 ካፒታል በጀት በሎት 1/የኩሬ ቁፋሮ ዙሪያ አጥርን ጨምሮ ሎት 2/ የንብ ማነብያ ዘመናዊ የንብ ቀፎ በዚሁ መሠረት በሎት 1 የኩሬ ቁፋሮ 10,000 ሜትር ክዩብ ሎት 2 የንብ ማነብያ ዘመናዊ የንብ ቀፎ የግልጽ ጨረታ ዘዴን በመጠቀም አወዳድሮ ለማሰራት እና ለመግዛት ይፈልጋል ::
1 በዚሁ መሠረት ፡- ከዚህ በታች ያለውን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
1/ የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው 2/ ተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ 3/ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው 4/ የግብር ከፋይነት ምስክር ወረቀት ያለው 5/ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ያለው፤
-
ለኩሬ ቁፋሮ WWC ደረጃ 5ና ከዛ በላይ ያለው፤
-
በዘርፉ 2 ዓመትና ከዚያ በላይ የሥራ ልምድ ያለው፤
-
የጨረታ ሠነድ ሲገዙ የማይመለስ 200 ብር ለእያንዳንዱ ሎት ገቢዎች ጽ/ቤት በመክፈል የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 30 ተከታታይ የሥራ ቀን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከወረዳው ፋይናንስ ጽ/ቤት ከግዥ ዋና ሥራ ሂደት ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
-
ጨረታው የግልጽ ጨረታ ዘዴን ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 30 የሥራ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ በ30ኛው ቀን በ5 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 5፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ዕለቱ ሰንበት ቀን ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
-
ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ከሌሎች አስፈላጊ የመጫረቻ ሠነድ ጋር በታሸገ ኤንቭሎፕ ኦሪጅናልና ኮፒውን ሠነድ ማህተም ስም ፣ አድራሻ ፡- ስልክ ፤ ፊርማ በማኖር ለየብቻ በማሸግ አበላ አባያ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥ ዋና ሥራ ሂደት በመቅረብ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን መጨመር አለባችሁ፡፡
-
ተጫራቶች በገዙት ሠነድ መሠረት የምወዳደሩበትን ዋጋ ቫት ያጠቃለለ መሆኑን ወይም አለመሆኑን መግለፅ ይኖርባቸዋል፡፡ ካልተጠቀሰ ቫት እንደተካተተ ተደርጎው ይወሰዳል፤
-
በጨረታው መጫረቻ ሠነድ ላይ በዋጋም ሆነ በሌላ ሲሞላ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡
-
ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ብር ለሎት -1 ብር 10,000 ለሎት-2 ብር 5,000 cpo/ በጥሬ ገንዘብ ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት፡፡
-
ለምድብ 1 ኩሬ ቁፋሮ የሚወዳደሩ ተጫራቾች ማቅረብ የሚገባቸው ማሽነሪዎች እስካባተር ዶዘር፣ ሎደር ደምፒ፣ ትራክ ለሎችንም ጥሬ ዕቃዎች በአይነት ፣ በመጠን ሙሉ ለሙሉ አቅርበው መሥራት የሚችል እና የማሽነሪዎች ሁኔታ የተጫራቹ ስለመሆናቸው በቂ መረጃ የሚያረጋግጥ ወይም የኪራይ ከሆነ ወቅታዊ የኪራይ ውል ማቅረብ አለበት፡፡
-
በምድብ -1 ለኩሬ ቁፋሮ ተወዳድረው ያለፈ ተጫራች የቅደመ ክፈያ ከመቀበሉ በፊት የቅደመ ክፍያ ዋስትና 30% በባንክ የተረጋገጠ cpo ማቅረብ አለበት፡፡
-
አሸናፊ ተጫራች የጨረታ ውል ማስከበሪያ የውሉን ዋጋ 10% በባንክ የተረጋገጠ cpo በየምድቡ ለተወዳደሩበት ለሁሉም ለየብቻ ማስያዝ/ማቅረብ አለባቸው::
-
አሸናፊው ተጫራች ውል በገባው መሠረት ንብረቱን አበላ አባያ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ማስረከብ አለበት፡፡
-
ኩሬ ቁፋሮ የሚወዳደሩ ተጫራቾች የመስክ ምልከታ ያደረጉበትን ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው፡፡
-
መሥሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ወይም አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ:- ስ.ቁ. 0913-33-67-12/09-41-05-51-54/09-16-86-05-22/09-10-92- 82-41/0913-24-14-79
በደቡብ ኢትዮጵያ ክ/በወላይታ ዞን የአበላ አባያ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
