የደሴ አካል ተሀድሶ ማእከል ለፊዚዮቴራፒና ለዊልቸር አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በደቡብ ወሎ መስ/ዞን ደሴ አካል ተሀድሶ ማዕከል
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የደሴ አካል ተሀድሶ ማእከል ለፊዚዮቴራፒና ለዊልቸር አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ፦
-
- የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ፣ የግብር መክፈያ ቁጥር /TIN/ ያለው የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ ፣ ሕጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሰትን የሚያሟላ ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ሰነዱን ቢሮ ቁጥር 7 መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ በሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ብር ሲ.ፒ.ኦ /ጥሬ ገንዘብ/ ማቅረብ አለባችሁ፡፡
- የጨረታ ውድድሩ የሚደረገው በሎት ነው፡፡
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ተከታታይ የሥራ ቀን ቀጥሎ በሚውለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ በዕለቱ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 7 ጨረታው ይከፈታል፡፡
- ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሁሉም ተጫራቾች በአካል ባይገኙም በዕለቱ የጨረታ ሰነዱ ተከፍቶ ከታየ በኋላ ተገቢው የጨረታ ማስከበሪያ መኖሩ ከተረጋገጠ ተጫራቹ በአካል ባይገኝም ጨረታው ይከፈታል፡፡
- የጨረታ አሸናፊው በተሰጠው የጨረታ ሰነድ /Specification/ መሰረት እቃዎቹን በራሱ ትራንስፖርት አጎጉዞ በሚመለከታቸው ባለሙያ እየተረጋገጠ ለማእከሉ ን/ክፍል በሞ/19 ገቢ ማድረግ ይጠበቅበታል ፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 7 በአካል በመገኘት ወይም በቢሮ ስልክ ቁጥር 033 312 49 56፣ 033 311 70 48 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በደቡብ ወሎ መስ/ዞን ደሴ አካል ተሀድሶ ማዕከል
