Tender Detail

Tender Details

  • Company በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ለቡ ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address Addis Ababa, Ethiopia, Phone: 011 844 8675
  • Website
  • Deadline10 Mar 2025, 5:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories

በንፋስ ስልከ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ለቡ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቋሚ እቃ ግዥ እና የቢሮ ፓርቲሽን ግዥ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ለቡ ፋይናንስ ጽ/ቤት


ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በንፋስ ስልከ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ለቡ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለ2017 በጀት ዓመት የሚያስፈልጉ እቃዎችን በግዢ መለያ ቁጥር 02/2017 ማለትም ሎት 01 ቋሚ እቃ ግዥ  ሎት 2 የቢሮ ፓርቲሽን ግዥ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

 ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ1. ለሎት 01 የጨረታ  ማስከበሪያ ብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር ብቻ ) 2. ለሎት 02 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 15,000 (አስራ አምስት ሺህ ብር ብቻ)

በባንክ በተረጋገጠ ሰነድ (CPO) ብቻ ከጨረታው ሰነድ ጋር በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ጥቃቅንና አነስተኛ ተወዳዳሪዎች በተመለከተ ባመረታችሁት ምርት ብቻ ወይም እሴት ተጨማሪ ባደረጋችሁበት ብቻ ከአደራጃቸው ክፍል ዋስትና በማፃፍ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ ወረዳው ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት፡-

  1. በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር ብቻ)በመክፈል ሰነዱን ከወረዳው ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 403 ቀርበው መግዛት ይችላሉ።
  3. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት ድረስ አየር ላይ ውሎ በ10ቀን ከቀኑ 11፡30 ታሽጎ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወረዳው ወጣት ማዕከል መሰብሰቢያ አዳራሽ ጨረታው ይከፈታል።
  4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት በወረዳው ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 403 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥማስገባት ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው ለሎት 01 በተያያዘው እስፔክ መሰረት የሚያቀርቡ ሲሆን፤ ለሎት 02 ደግሞ በአካል በመገኘት የሚሰራውን የፓርቲሽን ስራ በአልሙንየምእና ተመሳሳይ ምርቶች ማቅረብ አለባቸው። ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ለያንዳንዱ ከቫት ጋር ወይም ቲኦቲ ተካቶ ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል
  6. የዘገየ ጨረታና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም
  7. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈጻሚው መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  8. ወረዳው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ oı ለቡ ፋይናንስ ጽ/ቤት ሲትራ ህንፃ ወይም ከከቤ ኬክ ቤት 200ሜ ገባ ብሎ፡፡

ስለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-011 844 8675/ 011 844 1161ደውለው ይጠይቁ።

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ለቡ

ፋይናንስ ጽ/ቤት

Save Tender