በኢትዮጵያ ጉምሩከ ኮሚሽን የጅማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተገለፀውን የሰራተኞች የደንብ ልብስ፣ የፅህፈት መሣሪያ ዕቃዎች፣ የፈርኒቸር አቃዎች እና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በጉምሩክ ኮሚሽን ጅማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ ጉምሩከ ኮሚሽን የጅማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተገለፀውን የሰራተኞች የደንብ ልብስ፣ የፅህፈት መሣሪያ ዕቃዎች፣ የፈርኒቸር አቃዎች እና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ዕጩ ተወዳዳሪዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማለትም፡-
-
- የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው
- የዘመኑን ግብር የተከፈለበት ማስረጃ
- የግብር መለያ ቁጥር (TIN)
- የአቅራቢነት ማስረጃ
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያለው በጨረታው መሳተፍ የሚችል ሲሆን፤
- የጨረታው ሰነድ የሚገኝበት ቦታ :- ጉምሩክ ኮሚሽን ጅማ ቅ/ጽ/ቤት አድራሻ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስ ኤንድ ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ 200 ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘው የሰራተኞች ኮንፍድሬሽን ህንፃ አንደኛ ፎቅ ላይ የሚገኘው የግዥና ፋይናንስ አስተዳደር ክፍል፡፡ የጨረታውን ሰነድ ለመውሰድ የሚፈልግ ተጫራች የማይመለስ 100 (አንድ መቶ) ብር በካሽ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንከ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በ (Customs Commission Jimma Branch) ገቢ በማድረግ የደረሰኙን ኮፒ በፖስታ በማሸግ ጨረታው ከሚዘጋበት ሰዓት ቀደም ብሎ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያና ሌሎች ሰነዶችን ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት በመንግስት የስራ ሰዓት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ትችላላችሁ።
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ በ16ኛው ቀን በጉምሩከ ኮሚሽን ጅማ ቅ/ጽ/ቤት በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4፡30 ይከፈታል፡፡
- የመንግሥት መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፈል ወይም ሙሉ በሙሉ ለመሰረዝ መብት አለው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልከ ቁጥር፡- 047-211-34-52 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በጉምሩክ ኮሚሽን ጅማ ቅ/ጽ/ቤት
