የኦሮሞ ራስ አገዝ ማህበር (OSRA) መንግስታዊ ያልሆነ አገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ሸዋ ዞን ወሊሶ ወረዳ በድሬ ዱለቲ ቀበሌ ገበሬ ማህበር፤ በዳዎ ወረዳ ቡሣ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት፤ ቀርሳ ቀበሌ ገበሬ ማህበር እንደዚሁም ቀርሣ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት በጠቅላላው አራት መካከለኛ የመጠጥ ውኃ ጉድጓዶችን ለማስቆፈር ይፈልጋል፡፡
የኦሮሞ ራስ አገዝ ማህበር (OSRA)
የጨረታ ማስታወቂያ
የኦሮሞ ራስ አገዝ ማህበር (OSRA) መንግስታዊ ያልሆነ አገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ሸዋ ዞን ወሊሶ ወረዳ በድሬ ዱለቲ ቀበሌ ገበሬ ማህበር፤ በዳዎ ወረዳ ቡሣ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት፤ ቀርሳ ቀበሌ ገበሬ ማህበር እንደዚሁም ቀርሣ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት በጠቅላላው አራት መካከለኛ የመጠጥ ውኃ ጉድጓዶችን ለማስቆፈር ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉና በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ፡-
1. በዘርፉ የታደሰ የሥራ (ንግድ ፈቃድ) ያላቸው፤
2. ከዘመኑ ግብር ዕዳ ነጻ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
3. የጨረታ ማስከበሪያ ከሚያቀርቡት ዋጋ አንድ ፐርሰንት (CPO) ማስያዝ የሚችሉ፤
ዓለምገና ኦይል ሊቢያ የነዳጅ ማደያ በስተምስራቅ 200 ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘው ቢሯችን በመቅረብ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ለዚሁ የተዘጋጀውን TOR በመውሰድ የሚጫረቱበትን ዋጋና ቴክኒክ እንዲያስገቡ እንጠይቃለን፡፡
ጨረታው ማስታወቂያው በጋዜጣ በወጣ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት በድርጅቱ ዋና መ/ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ በሌላ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251-11-367-91-01/02 ዘወትር በሥራ ሰዓት ደውለው መረዳት ይችላሉ።
የኦሮሞ ራስ አገዝ ማህበር (OSRA)
