በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የእንስሳት ሕክምና እና ግብርና ኮሌጅ እንሰሳት ምርምር እና ዕርባታ ማዕከል የ2017 ዓ.ም ለእንሰሳት መኖነት የሚገለግሉ የድርቆሽ ሳር ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመፈጸም ይፈልጋል።
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የእንሰሳት ሕክምና እና ግብርና ኮሌጅ
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር እ/ህ/ግ/ኮ 004/2017
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የእንስሳት ሕክምና እና ግብርና ኮሌጅ እንሰሳት ምርምር እና ዕርባታ ማዕከል የ2017 ዓ.ም ለእንሰሳት መኖነት የሚገለግሉ የድርቆሽ ሳር ግዥ የወጣ ግልፅ ጨረታ ሲሆን
ስለሆነም :-
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና ህጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያላቸው እንዲሁም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለሥልጣን የታክስ ከፋይ (Tin No) የምስክር ወረቀት የአቅራቢዎች ምዝገባ /supplier list እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል የተሰጠ ማስረጃ መሆን አለባቸው ::
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር (40,000.00) /አርባ ሺህ ብር/ በጥሬ ገንዘብ ወይም ከታወቀ ባንከ በሚሰጥ የከፍያ ማዘዣ ቼክ ወይም የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቢሾፍቱ ከተማ በሚገኘው የእንሰሳት ሕክምና እና ግብርና ኮሌጅ ግዥ ክፍል በመቅረብ መዉሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን የያዘውን ሰነድ አንድ ቴክኒካል ኦሪጂናልና አንድ ቴክኒካል ኮፒ እና አንድ ፋይናንሽያል ኦርጅናልና አንድ ፋይናንሽያል ኮፒ በእናት ፖስታ በማድረግ ጨረታዉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት እስከ 16ኛው ቀን 7፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በኮሌጁ ግዥ ክፍል በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
- ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን በ7፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት በ8፡00 ሰዓት በግልፅ ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ የህዝብ በዓል ቀን ከዋለ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን ከላይ በተገለፀዉ መዝጊያ ሰዓት ታሽጎ በግልጽ ይከፈታል፡፡
- በጨረታ መክፈቻ ቀኑ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባይገኙም ጨረታዉ ከመከፈት አይስተጓጎልም፡፡
- ተጫራቾች የአሸነፏቸውን አቅርቦቶች በሚሰጣቸው ትዕዛዝ መሰረት በቢሾፍቱ ከተማ በሚገኘው የእንስሳት ሕክምና እና ግብርና ኮሌጅ ዕቃ ግምጃ ቤት ድረስ በራሳቸው ትራንስፖርት በማጓጓዝ ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር - 0114338557 / 0912065392
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የእንሰሳት ሕክምና እና ግብርና ኮሌጅ
ቢሾፍቱ
