የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮምሽን ለ2017 በጀት ዓመት ለሰራዊቱ አገልግሎት የሚውል ቦት ጫማ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
Dire Dawa Administration Police Commission (የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን)
የጨረታ ማስታወቂያ
የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮምሽን ለ2017 በጀት ዓመት ለሰራዊቱ አገልግሎት የሚውል ቦት ጫማ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች
- የጨረታውን ሠነድ የማይመለስ ብር 300/ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ለ15 ተከታታይ ቀናት በድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ፋይናንስና ግዥ ዳይሬክቶሬት የሥራ ሒደት ቢሮ ቁጥር 16 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የዘመኑን የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር ከፋይ የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆንና የጨረታውን ውጤት እንደታወቀ የሚመለስ የሚጫረቱበትን እቃ ዋጋ 2% CPO/ወይም ጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- በተዘጋጀው የጨረታ ሠነድ ላይ ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ተመራጭነት አለው፡፡
- የቴክኒካል ሰነድ እና የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት ለየብቻ በማሽግ ከአንድ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ በጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታውን ሰነድ 25/3/2017 እስከ 09/4/2017 ዓ.ም ከቀኑ 11:00 ሰዓት ድረስ በድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን በፋይናንስና ግብር አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 16 ቀርበው መግዛት ይችላሉ።
- ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 10/4/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሣጥኑ ታሽጎ 3፡30 ሠዓት ይከፈታል፡፡
- ፖሊስ ኮሚሽን የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር +251-0111-74-55 በመደወል መረጃ ፖ.ሣ.ቁጥር 1453 ማግኘት ይችላሉ፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን
