የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች እና አገልግሎቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት/ ለማሰራት ይፈልጋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ
የጨረታ ማስታወቂያ
የግዢው መለያ ቁጥር: - ВОНЕА-PPAD-NCB-Recurrent Budget-2017-2nd BID
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች እና አገልግሎቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት/ ለማሰራት ይፈልጋል።
|
ምድብ |
የግብዓቱ /አቃው/ አገልግሎቱ አይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
|
ሎት አንድ |
የፅህፈት መሳሪያዎች |
4000 |
|
ሎት ሁለት |
የፅዳት እቃዎች |
4000 |
|
ሎት ሶስት |
የሰራተኞች የደንብ ልብስ |
3000 |
|
ሎት አራት |
የሠራተኞች የደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት |
1500 |
|
ሎት አምስት |
የፕሪንተር እና የፎቶ ኮፒ ማሽን ቶነር |
18000 |
|
ሎት ስድስት |
ጀነሬተር 40 KVA |
50000 |
|
ሎት ሰባት |
የሊፍሌት ዲዛይን፣ ሕትመት፣ የቪዲዮ ክሊፕ መስራት |
8000 |
|
ሎት ስምንት |
የተለያዩ ፈርኒቸሮች እና ቋሚ እቃ የአበባ ማስቀመጫ እና መታወቂያ ፕሪንት ማድረገያ |
8000 |
|
ሎት ዘጠኝ |
አዲስ አበባ ውስጥ የሆቴል አዳራሽ እና መስተንግዶ አገልግሎት የአንድ አመት ውል (በድጋሚ የወጣ) |
20000 |
|
ሎት አስር |
ለተለያዩ ተሽከርካሪዎች ጎማ እና ባትሪ |
50000 |
|
ሎት አስራ አንድ |
የተሸከርካሪ አልባሳት |
15000 |
|
ሎት አስራ ሁለት |
የተለያዩ ሕትመት አገልግሎት |
5000 |
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት የሚያቀርቡ ብሎም በአሁኑ ሰዓት ያሉ መሆን አለባቸው፡፡
- የቫት ተመዝጋቢ ሆነው ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉና መለያ ቁጥር /ቲን ነበር ያላቸው መሆን አለበት።
- ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና በዘርፉ የተሰማሩ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከላይ የተጠቀሰውን ብር በየሎቱ ለየብቻ CPO ወይም BOND ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት በየሎቱ ብር 100 በየሎቱ በመክፈል ከመንግሥት ግዢ ዳይሬክቶሬት አስከ 10ኛው የስራ ቀን ድረስ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ እስከ 11ኛው የስራ ቀን 3፡45 ድረስ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ዋጋ ሞልቶ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተምና ፊርማ አድርጎ ያላቀረበ ተጫራች ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የመጫረቻ ሰነድ ፋይናንስ ዋና እና አንድ ኮፒ እንዲሁም ቴክኒካል ዋና እና አንድ ኮፒ ለየብቻ በማድረግ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ቢሮው በጨረታ ሰነዱ ከተገለጸው የዕቃ/ የአገልግሎት ፍላጎት መጠን ጨረታ ሰነዱ ላይ ከውል በፊት 20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
- ጨረታው ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ 90 ቀናት ነው፡፡
- ጨረታው የሚዘጋበት ቀን የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣ ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን ጠዋት 3፡45 ታሽጎ በዕለቱ 4፡15 በመ/ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ይሆናል፡፡
- ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 01 ማህበራዊ ዋስትና አዲሱ ህንፃ /ማህበራዊ ዋስትና የንግድ ማእከል ህንፃ 7ኛ ፎቅ (ፒያሳ ኤንሪኮ ኬክ ቤት አካባቢ/ የመንግስት ግዢ ዳይሬከቶሬት
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር -- 011-8-33-25-01
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ
