Tender Detail

Tender Details

  • Company Debre Markos University (ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ)
  • Address ደብረ ማርቆስ ከተማ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 058-771-66-91
  • Websitehttp://www.dmu.edu.et/
  • Deadline08 Dec 2024, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Kitchen Materials

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በ2017 በጀት አመት ከመንግስት በተፈቀደለት በጀት ለተማሪዎች ምግብ ቤት ለምግብ ዝግጅት ስራ የምንጠቀምባቸው እቃዎች በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

Debre Markos University (ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ)


የጨረታ ማስታወቂያ

ደ/ማ/ዩ/ብግጨ/09/2017

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በ2017 በጀት አመት ከመንግስት በተፈቀደለት በጀት ለተማሪዎች ምግብ ቤት ለምግብ ዝግጅት ስራ የምንጠቀምባቸው እቃዎች በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም  በጨረታው  መሳተፍ  የሚችሉ  ከዚህ  በታች  ማለትም፤

  1. በዘመኑ እና በአርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ እና የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ እና የግብር ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  2. ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ማለትም ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይንም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ስም አሰርቶ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች ሁሉ የጨረታ ዶክመንቱ ደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ህንፃ ቁጥር 27 ቢሮ ቁጥር 10 ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
  3. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 21 ቀን አየር ላይ ቆይቶ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚያው እለት ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  4. የጨረታውን ፋይናንሽያል ዶክመንት እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያውን ለየብቻ አስተማማኝ በሆነ ማጣበቂያ በታሸገ ፖስታ በማድረግና በእያንዳንዱ ፖስታ ላይ የመ/ቤቱን ሙሉ ስምና አድራሻ በመፃፍ ማህተም በማድረግ በተጠቀለለ አንድ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  5. አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ በተገለፀለት ከ7 ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ በግንባር ቀርቦ አሸናፊ የሆነበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ በ8 ቀናት ውስጥ ውል መያዝ አለበት።
  6. ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነዱን በአግባቡ በመሙላትና በማሸግ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ህንፃ ቁጥር 27 ቢሮ ቁጥር 10 ድረስ በመቅረብ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከተከታታይ 21 ቀናት በኋላ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡59 ድረስ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው ጨረታው በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡30 ሰዓት ላይ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ህንፃ ቁጥር 27 ቢሮ ቁጥር 10 ውስጥ ይከፈታል።

ሆኖም ተጫራቾች በጨረታው ላይ መገኘት ካልቻሉ መስፈርቱን እስካሟሉ ድረስ በጨረታው ላይ ያልተገኙ ተጫራቾች ፖስታ ጨረታ በእለቱ ይከፈታል።

የበለጠ መረጃ ለማግኘት በስልክ ቁጥር 058 771 66 91 /058/178 00 37/ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

  • የጨረታ መክፈቻ ቀኑ የበአል ቀናት ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።

ዩኒቨርሲቲው ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

 

Save Tender