በቤ/ጉ/ክ/መ/የማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ዞን ማ/ቤቶች መምሪያ በህግ ጥላ ስር ለሚገኙ የህግ ታራሚዎች ከህዳር 15/2017 ዓ.ም እስከ ሚያዝያ 15/2017/ ዓ.ም የስድስት ወር (6) ወር የምግብ ፍጆታ እና የወጥ ማጣፈጫ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ደፈልጋል፡፡
የቤ/ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት የማ/ቤቶች ኮሚሽን የካማሽ ዞን ማ/ቤቶች መምሪያ ካማሽ
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ፡- 002/2017/ዓ.ም
በቤ/ጉ/ክ/መ/የማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ዞን ማ/ቤቶች መምሪያ በህግ ጥላ ስር ለሚገኙ የህግ ታራሚዎች ከህዳር 15/2017 ዓ.ም እስከ ሚያዝያ 15/2017/ ዓ.ም የስድስት ወር (6) ወር የምግብ ፍጆታ እና የወጥ ማጣፈጫ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ደፈልጋል፡፡ በዚህ መሠረት በሥራ ዘርፉ ፈቃድ አውጥታችሁ በሥራ ላይ የተሰማራችሁ ሁሉ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሰነዶቹን መግዛትና መጫረት ትችላላችሁ።
- የጨረታ ምዝገባ እና መክፈቻ ቦታ እንዲሁም አቅርቦት በቤ/ጉ/ክ/መ ካማሺ ኮን በካማሺ አዳራሽ ይሆናል።
- በተጠቀሰው የሥራ ዘርፍ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለውና የዘመኑን ግብር የከፈለ
- የንግድ ፍቃድና የምስከር ወረቀት ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችል የግብር መለያ ቁጥር /Tin No/ ያለው
- ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነና ከሚመለከተው የገቢዎች ባለስልጣን መ/ቤት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ካማሺ ዞን ማ/ቤቶች መምሪያ ቢሮ ቁጥር 12 ድረስ በመምጣት የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለምግብ ፍጆታ የጨረታ ማስያዣ ብር 5.000.00/አምስት ሺህ ብር/ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በሲፒኦ /CPO/ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ዝርዝር ስርዝ ድልዝ ያለበት ሆኖ ከተገኘ ተጫራቾች /ድርጅቱ/ ወዲያውኑ ከጨረታው ውጪ ይደረጋል፡፡
- በሰነዱ በተቀመጠው ዝርዝር ላይ ከተራ ቁጥር 1፣2፣3፣5፣6፣7፣8፣9፣10፣13፣15፣19፣20 እና 23 ላይ ያሉት የመኖ ቀለብ ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታውን ላሸነፉ ተጫራቾች /ድርጅቶች/ መስሪያ ቤቱ ያስያዙትን ሲፒኦ /CPO/ ወዲያውኑ የሚመልስ ሲሆን የአሸናፊው /ድርጅት/ ሲፒኦ /CPO/ ግን ከመ/ቤቱ ጋር በሚገባው ውል መሰረት ይያዛል፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱን እና የውል ስምምነቱን በመውሰድ በመሙላትና በዝርዝር በማስቀመጥ ኦሪጅናል እና የማይመለስ ፎቶ ኮፒውን በመለየት በታሸገ ኤንቨሎፕ ወይም ፖስታ ውስጥ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው ማስታወቂያው በ16ኛው ቀን ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ላይ የሚከፈት ሲሆን ቅዳሜና የበዓል ቀናት ሲገጥም ወደ ሥራ ቀናት ይሻገራል፡፡
- ተጫራቾች የተጠቀሱትን የሰነዱ ዝርዝሮች ላይ መ/ቤቶች 20% የመጨመርም ሆነ የመቀነስ መብት አለው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ባይገኙ የጨረታውን መክፈት ሂደት አያስተጓጉልም፡፡
- መ/ቤቱ አማራጭ /የተሻለ/ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ ፡ የካማሺ ዞን ማ/ቤቶች ድረስ ቀርበው መረጃ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን በስልክ ቁጥር 0913435313 / / 0917444895 / 0911510798 በመደወል ጠይቀው መረዳት ይችላሉ፡፡
የቤ/ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት የማ/ቤቶች ኮሚሽን
የካማሽ ዞን ማ/ቤቶች መምሪያ
ካማሽ
