የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት የካፌ አገልግሎት በግልፅ ጨረታ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት
የጨረታ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት የካፌ አገልግሎት በግልፅ ጨረታ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ከ6 ኪሎ ወደ ፒያሳ የሚወስደው መንገድ ላይ አፍንጮ በር ፍቅር ፕላዛ በሚገኘው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 306 በመምጣት የካፌ አገልግሎት ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ተገኝተው መግዛት ይችላሉ፡፡
- በዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ ስር በፊደል ያለ ስርዝ ድልዝ ገልፀው በታሸገ ኤንቨሎፕ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 405 ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ከ27/2/2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ተገኝተው ማስገባት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ 10,000 (አስር ሺ ብር) ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ሳጥን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን ህዳር 11/03/2017 ዓ.ም 11ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 405 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኙ በመቅረታቸው የጨረታውን እከፋፈት አያስተጓጉልም።
- ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ተካፋይ ሆኖ ጨረታው ከተዘጋ በኋላ ከጨረታው መውጣት ወይም የሰጠውን ዋጋ ማሻሻል ወይም መለወጥ አይችልም።
- የጨረታ ሳጥን ከታሸገ በኋላ የሚመጡ ማናቸውም ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
- አገልግሎቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 011-5-57-31-76 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት
