የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለጃንሜዳ G+3 ሰላም ማስከበር እና ድሬዳዋ ፌዴራል ፓሊስ ፈጥኖ ደራሽ ግንባታ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውል የSupply and fix Satellite dish system እና Ceramic and Porcelain tiles ግዥ አስመልክቶ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር DCE/SF/120/2024 እና DCE/CP/121/2024
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለጃንሜዳ G+3 ሰላም ማስከበር እና ድሬዳዋ ፌዴራል ፓሊስ ፈጥኖ ደራሽ ግንባታ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውል የSupply and fix Satellite dish system እና Ceramic and Porcelain tiles ግዥ አስመልክቶ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የዕቃው አይነት |
የፕሮጀክት ስም |
የጨረታ ቁጥር |
የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት |
የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
|
1 |
Supply and fix Satellite dish system |
ለጃንሜዳ G+3 ሰላም ማስከበር ግንባታ ፕሮጀክት |
DCE/ SF/120/2024 |
ህዳር 18/2017 ዓ.ም 4፡00 |
ህዳር 18/2017 ዓ.ም 4፡15 |
100,000.00 |
|
2 |
Ceramic and Porcelain tiles |
ድሬዳዋ ፌዴራል ፓሊስ ፈጥኖ ደራሽ ግንባታ ፕሮጀክት |
DCE/ CP/121/2024 |
ህዳር 18/2017 ዓ.ም 4፡15 |
ህዳር 18/2017 ዓ.ም 4፡30 |
100,000.00 |
ስለሆነ፡-
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፤ የግብር ከፋይ ምዝገባ፤ የታደሰ ታክስ ክሊራንስ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር ለእያንዳንዱ ጨረታ 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- አንድ ተጫራች መወዳደር የሚችለው በአንድ ዓይነት ምርት /ሞዴል/ ብቻ ነው። በአማራጭ የቀረበ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሰነዱ በተጠቀሰው ብዛት እና እስፔሲፊክሽን መሠረት መሆን ይኖርበታል። .
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ጨረታ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ቃሊቲ ቶታል ከአዲሱ ስታዲየም ጀርባ ወይም ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ት/ቤት አጠገብ በሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዋና መ/ቤት የግዥና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ መግዛት ይችላል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ቴክኒካል ሰነድ እና ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው ቀንና ሰዓት በኢንተርፕራይዙ የግዥና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታዎቹ በሰንጠረዡ በተገለፀው መሠረት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
- ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡-
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
ቃሊቲ ቶታል አዲሱ ስታዲየም ጀርባ ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ ት/ቤት አጠገብ
የቀጥታ ስልክ ቁጥር፡- 0114-40-34-34
ማዞሪያ፡- 0114-42-22-70/71/72
E-mail አድራሻ፡- Info@dce-et.com
የድረ ገፅ አድራሻ ፡-www.dce.gov.com/www.et.com
ፓ.ሳ.ቁ. 3414 ፋክስ ቁ. 011440-04-71/0114-42-07-46
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
