የነቀምቴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ለ 2017 ዓ.ም በጀት ዓመት ለተማሪዎች ምግብ የሚውል ጥራጥሬ ፣ ብዕር እህሎች፣ ፍራፍሬ፣ ሥጋ፤ የንጽህና መሳሪያዎች፣ ማገዶ /ግንድላ/ እና ማጣፈጫ ቅመማ ቅመሞች ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የነቀምቴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ
በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የነቀምቴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ለ 2017 ዓ.ም በጀት ዓመት ለተማሪዎች ምግብ የሚውል ጥራጥሬ ፣ ብዕር እህሎች፣ ፍራፍሬ፣ ሥጋ፤ የንጽህና መሳሪያዎች፣ ማገዶ /ግንድላ/ እና ማጣፈጫ ቅመማ ቅመሞች ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑ ግብር የከፈሉና ለተጨማሪ እሴት ታክስ እና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው::
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 15 የመንግስት ስራዎች ቀን ለእያንዳንዱ ሰነዶች የማይመለስ ብር 1000.00 /አንድ ሺህ ብር ብቻ/ በመክፈል ከነቀምቴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር 22 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ጥሩ የአቅራቢነት ባህርይ ያላቸው መሆን አለባቸው::
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት እህሎች ጥራት ያለውና ደረጃውን የጠበቀ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ማስከበሪያ ዋስትና 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ ብቻ ከታወቀ ባንክ ተረጋግጦ በሚቀርብ ሲፒኦ የአንድ ፖስታ ጋር በሰም በታሸገ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የዋጋ ዝርዝር የተጠቀውን / "Specification" ሳይለውጡ የጨረታ ማወዳደሪያ ሰነድ ላይ ዋጋውን በመሙላት ስማቸውን፣ ፊርማቸውንና አድራሻቸውን በማስፈር ማህተም በማድረግ የጨረታ ዶከመንታቸውን ኦሪጅናል ቴክኒክና ፋይናንስ በተለያዩ ፖስታ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በአንድ ትልቁ ፖስታ እስከ 11/03/2017 ዓ.ም ድረስ በቢሮ ቁጥር 22 በተዘጋጀው ሣጥን ጨረታው ከመዘጋቱ ከ1፡30 ሰዓት በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 12/03/2017 ዓ.ም በ 4፡00 ሰዓት ይከፈታል። ይሁን እንጂ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታውን ከመክፈት እያግደውም።
- የጨረታው ሳጥን ከታሸገ ወይም ከተከፈተ በኋላ የሚቀርብ ማንኛውም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
- የጨረታው አሸናፊ ተጫራቶች ከውል ሰጪው መ/ቤት ጋር በሚያደርገው የውል ስምምነት መሰረት ነቀምቴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ በሚገኘው ከውል ሰጪው ንብረት ክፍል ገቢ ያደርጋል፡፡
- መ/ቤታችን በሚያወዳድረው እህሎች ሆነ ሌሎች የተጠየቀውን "Specification" ብዛት ላይ እንደየአስፈላጊነቱ 20% መጨመርና መቀነስ ይችላል፡፡
- ተጫራቾች ካሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቶች ጨረታውን አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀ ከአምስት ቀን በኋላ በውል ሰጪው መ/ቤት ድረስ በአካል በመገኘት የውል ስምምነት የመፈፀም ግዴታ አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች ጨረታውን ከአሸነፉ በኋላ የገበያ ዋጋ ጨምሯል ብለው ማመልከቻ የሚያቀርቡ ከሆነ ተቀባይነት የለውም፡፡
ማሳሰቢያ
ዋጋ ከመስጠትዎ በፊት መመሪያውን በትክክል ያንብቡ
ስልክ ቁጥር፡- 05-76-60-13-02/09-17-08-75-17
የነቀምቴ መምህራን ትምህር ኮሌጅ
