በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ስር የሚገኘው እቴጌ መነን የልጃገረዶች አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
Addis Ababa Education Bureau (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር /001/17
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ስር የሚገኘው እቴጌ መነን የልጃገረዶች አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
|
1. የተለያዩ ቋሚ ዕቃዎች፤ 2. የጽዳት ዕቃዎች የእንስሳት መኖ፤ 3. የጽህፈት መሳሪያዎች፤ 4. የደንብ ልብስ እና የደንብ ልብስ ስፌት፤ 5. የተለያዩ የትምህርት ዕቃዎች፤ 6. የተለያዩ የስጦታ ዕቃዎች፤ 7. የጥገና ዕቃዎች፤ 8. የፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ ኪራይ መኪና፤ 9. በት/ቤት ግቢ ውስጥ ያሉ የተለያዩ የጥገና ሥራዎች፤ |
10. 60 ሰው መያዝ የሚችል ዘመናዊ አውቶቢስ ኪራይ፤ 11. የመኪና ዕቃዎች፣ 12. የማሽነሪ ዕቃ ጥገና እና ሰርቪስ፤ 13. የእንስሳ ህክምና፤ 14. የተለያዩ እጽዋቶች፤ 15. ህትመት፤ 16. የህክምና ዕቃዎች ቋሚና አላቂ፤ 17. ለምርምር የሚሆኑ ዕቃዎች፤
|
- ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤
- የታደሰ ንግድ ፈቃድ ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ መሆናቸውን ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ እና ከፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶሰት መቶ ብር) በየሎቱ በመክፈል ከት/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 103 መግዛት ይችላሉ፡፡ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት 1ኛ ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታውን ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን ኤንቨሎፕ ለዚህ በተዘጋጀ የጨረታ ሣጥን ውስጥ ቢሮ ቁጥር 11 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም ጨረታው እስከሚከፈት ድረስ የዕቃ ናሙና መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊው በሚያቀርባቸው ዕቃዎች ላይ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- ጨረታው 11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ4፡30 ሰዓት ቢሮ ቁጥር 111 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ት/ቤቱ ባቀረበው የዋጋ መሙያ ብቻ በመሙላት ማቅረብ እና ያሸነፉበትን ዕቃ በራሳቸው ትራንስፖርት ት/ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ት/ቤቱ የሚገዛውን ዕቃ ብዛት 20% የመጨመርና የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፤፤
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር ለሎት 1 ብር 4,000.00 እና ለሎት 2 3,000.00 ለሎት 3፡4:5:6:7፡8 2,000.00 ለሎት 9 30,000 ባንከ የተረጋገጠ ክፍያ አቅርቦት (CPO) በፖስታው ውስጥ አብረው ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጥቃቅንና አነስተኛ ተወዳዳሪዎች የሚወዳደሩት በሚያመርቱት ምርት ካልሆነ በስተቀር ዕቃ ገዝተው የሚያቀርቡ ከሆነ እንደማንኛውም ተጫራቾች ሰነድ በመግዛትና ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታ የሚሳተፉ አካላት ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ (ማብራሪያ) ከፈለጉ በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 0111261615 /0111 22 49 54/56 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡ እንዲሁም የሚሰሯቸውን ስራዎች በሙሉ በአካል ት/ቤቱ በመገኘት ሳንፕል መውሰድ ማየት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በአንድ የዕቃ አይነት በአንድ ብራንድ ብቻ መወዳደር ይኖርባቸዋል፡፡
አድራሻ፡- እቴጌ መነን የልጃገረዶች አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ከ6 ኪሎ ዩኒቨርሲቲ - በግራ በኩል በሚወስደው መንገድ ወይም ምስካዬ ኅዙናን መድሃኒያለም ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ገባ ብሎ ይገኛል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የእቴጌ መነን
የልጃገረዶች አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት
