በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በለሚ ኩራ ከ/ከተማ በወረዳ 6 ስር የሚገኘው የቤኬ ቅድመ አንደኛና አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2017 የበጀት አመት የሚያስፈልጉ ግብአቶችን ማለትም ሎት1 የደንብ ልብሰ ሎት2 አላቂ የፅህፈት መሳሪያዎችና የቢሮ እቃዎች ሎት3 ህትመት ሎት4 አላቂ የትምህርት እቃዎች ሎት5 የፅዳት እቃዎች ሎት6 ልዩ ልዩ መሳሪያዎች፤ ሎት7 ኤሌክትሮኒከስ እቃዎች ሎት8 ቋሚ የቢሮ እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::
የለሚ ኩራ ክ/ከተማ የቤኬ ቅድመ አንደኛና አንደኛ ደረጃ ት/ቤት
የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በለሚ ኩራ ከ/ከተማ በወረዳ 6 ስር የሚገኘው የቤኬ ቅድመ አንደኛና አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2017 የበጀት አመት የሚያስፈልጉ ግብአቶችን ማለትም ሎት1 የደንብ ልብሰ ሎት2 አላቂ የፅህፈት መሳሪያዎችና የቢሮ እቃዎች ሎት3 ህትመት ሎት4 አላቂ የትምህርት እቃዎች ሎት5 የፅዳት እቃዎች ሎት6 ልዩ ልዩ መሳሪያዎች፤ ሎት7 ኤሌክትሮኒከስ እቃዎች ሎት8 ቋሚ የቢሮ እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::
በዚህ መሰረት በጨረታ መሳተፍ የምትፈልጉ፡-
- ለተጠቀሱት እቃዎች በዘርፉ የንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ መሆን አለባቸዉ፡፡
- የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድና በአቅራቢነት የተመዘገቡበት የምዝገባ ሰርትፊኬት ያላቸዉ።
- የዘመኑን ግብር ስለ መክፈላቸው ከሚመለከተዉ አካል መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ከሆኑ ሰርትፊኬት ማቅረብ የሚችሉ።
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /ቲን ሰርተፍኬት/ ያላቸዉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ከላይ የተዘረዘሩትን ሰነዶች አርጅናልና ኮፒ ለየብቻ በመለየት ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በፖስታ በማሸግ ማስገባት አለበት ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ በባንክ በተረጋገጠ የ10,000 የኢትዮጲያ ብር (CPO) ሲፒኦ ለሁሉም ሎቶች ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ አሸናፊ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- ለጨረታ ሰነዱ የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ጨረታ ሰነድ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በት/ቤቱ ፋይናንስ ክፍል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የተጫረታችሁበትን እቃ ወይም ሎት 1 እስከ ሎት 8 መጫረት ወይም መርጠው አንዱን ወይም ሁለቱን መጫረት ይችላሉ ነገርግን ከያንዳንዱ ሎት እቃዎች መራርጠው ለተወሰኑት እቃዎች ብቻ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ተጫራቾች የምትጫረቱበትን እቃ በሎት1 --- ለሎት2 --- ለሎት3 --- ለሎት4 --- ለሎት5 እና ለሎት6 ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ አንድ ቀን በፊት ማቅረብ አለባችሁ። ለሎት7 እና ለሎት8 ደግሞ እስፔስፍኬሽኑን (ሰነዱን) መሰረት ያደረገ ፎቶ ማስገባት አለባችሁ።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ለእያንዳንዱ ቫትን ጨምሮ ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የዘገየ ጨረታና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፏቸውን እቃዎች በራሱ በአሸናፊው ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚው መ/ቤት ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
- ተጫራቶች የምታቀርቡትን ዋጋ በዝርዝር በሰነዱ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ በግልፅ ሞልታችሁ በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን በስራ ሰዓት ለዚህ ጨረታ ማስገቢያ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ኮፒና ኦርጅናል ለየብቻ በፖስታ በማሸግ በቤኬ ቅድመ አንደኛና አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ማስገባት አለባችሁ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ በ11ኛው ቀን በ3፡30 (አስር ሰዓት ተኩል) ታሸጎ በእለቱ በ4፡00 (አራት ሰዓት) ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ተጫራቹ /ህጋዊ ወክል ያለመገኝት የጨረታ አከፋፈት ላይ ተጽኖ አያመጣም፡፡ 11ኛው ቀን የበአል ቀን ወይም የእረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል ፡፡
- ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
- የት/ቤቱ አድራሻ ፡- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክ/ከተማ በወረዳ 6 ስር የሚገኘው የቤኬ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ከሰፈራ አደባባይ ወደ ባታ ማርያም በሚወስደው ዋና መንግድ ላይ ያገኙናል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክ/ከተማ የቤኬ ቅድመ
አንደኛና አንደኛ ደረጃ ት/ቤት
