Tender Detail

Tender Details

  • Company የባሌ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Address , Phone: 022-665-0225
  • Website
  • Deadline09 Nov 2024, 9:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Food And Beverage

የባሌ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት በጉራዳሞሌ ወረዳ ስር ለሚገኙ ትምህርት ቤቶች የሚያገለግሉ የተማሪዎች ቀለብ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የባሌ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት


የጨረታ  ማስታወቂያ  የጨረታ  ቁጥር  ባ/ዞ/

ገን/ጽ/ቤት 02/2017

የባሌ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት በጉራዳሞሌ ወረዳ ስር ለሚገኙ ትምህርት ቤቶች የሚያገለግሉ የተማሪዎች ቀለብ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ የንግድ ድርጅቶች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።

  1. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት የምግብ እህል አቅርቦት የሚያገለግል ለ2016/2017 ዓ.ም. የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃዳቸውን (Trade license) : የንግድ ምዝገባ ወረቀት:የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) : የግብር ከፋይ መለያ (TIN) ሰርተፍኬት ፤ የአቅራቢነት ምዝገባ ማስረጃ ( Supplier list ) ማቅረብ ይኖርባቸል፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ የሰነድ መሸጫ ዋጋ 100 ብር በባሌ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ስም በተከፈተው የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1069593281212 በስንቄ ባንክ በማስገባት ሰነዱን ከባሌ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ከቢሮ ቁጥር 15 በመግዛት እና የጨረታ ማስከበሪያ 50000.00 ( ሃምሳ ሺህ ብር)  በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ በባሌ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ስም በማስያዝ መወዳደር ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት የስራ ቀን ጀምሮ የሚጫረቱባቸውን ሰነዶች በመግዛት ኦሪጂናል (ዋናውን) ፋይናንሺያል ( ዋጋ የተሞላበት) ሰነድ እና ቴክኒካል ኦሪጂናል ሰነድ ሁለቱንም ሰነድ በተለያዩ ፖስታዎች አሽገው ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰአት የጨረታው ሳጥን እስከሚታሸግበት እለት እና ሰአት ድረስ ማስገባት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በባሌ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ስም ያስያዙትን ሲፒኦ ከቴክኒካል ኦሪጂናል ሰነድ ጋር አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. እያንዳንዱ ሰነድ እና የታሸገ ፖስታ ላይ የድርጅቱ ኃላፊ ፊርማ እና ማህተም መኖር አለበት፡፡
  6. ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ዕለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡
  7. ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገለፀላቸው ከ5ኛው ቀን በኋላ ከ6ኛው ቀን ጀምሮ በ15 የስራ ቀናት ውስጥ ባሌ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ቀርበው ውል መፈራረም አለባቸው፡፡
  8. ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ::

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልከ ቁጥር 022-665-0225 ደውለው ይጠይቁ።

 

የባሌ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት

Save Tender