የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በ2017 በጀት አመት ለዋናው ግቢ፣ ለጤናና ህክምና ካምፓስና ለቡሬ ካምፓስ የተማሪዎች ምግብ አገልግሎት የሚውሉ ግብዓቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር- ብግጨ 07/2017
የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በ2017 በጀት አመት ለዋናው ግቢ፣ ለጤናና ህክምና ካምፓስና ለቡሬ ካምፓስ የተማሪዎች ምግብ አገልግሎት የሚውሉ ግብዓቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ ከዚህ በታች በተገለፀው ማለትም፡-
- በዘመኑ እና በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ የታክስ ክሊራንስ ለግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ እና የተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ1 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሠነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ዋጋ ሞልተው ሲመልሱ ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን
- ሎት 1:- ስጋ ብር 50.000 /ሃምሳ ሺህ ብር/
- ሎት 2 - እንጀራ ብር 80.000.00 /ሰማኒያ ሺህ ብር/
- ሎት 3- ቀላጭ ዘይት 60.000.00 /ስልሳ ሺህ ብር/
- በባንክ በተረጋገጠ ሲፒአ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ስም አሰርቶ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ሁሉ የጨረታ ዶክመንቱን ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ህንፃ ቁጥር 27 ቢሮ ቁጥር 10 እና አዲስ አበባ አራት ኪሎ ከቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ወረድ ብሎ ሮሚና ካፌ ህንፃ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 07 ድረስ በመቅረብ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የማይመለስ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በዩኒቨርስቲ ሂሳብ ቁጥር 1000017980517 ንግድ ባንክ ገቢ በማድረግ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተወዳዳሪ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአግባቡ በመሙላትና በማሸግ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡59 ሰዓት ድረስ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ህንፃ ቁጥር 27 ቢሮ ቁጥር 10 ድረስ በመቅረብ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው::
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ህንፃ ቁጥር 27 በግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 10 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች በጨረታው ላይ መግኘት ካልቻሉ መስፈርቱን እስካሟሉ ድረስ በጨረታው ላይ ያልተገኙ ተጫራቾች ፖስታን ጨምሮ ጨረታው በእለቱ ይከፈታል፡፡
- የጨረታውን ፋይናንሽያል ኦሪጅናል ቴክኒካል ዶከመንቶች እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያውን ለየብቻ አስተማማኝ በሆነ ማጣበቂያ በታሸገ ፖስታ በማድረግና በእያንዳንዱ ፖስታ ላይ የመ/ቤቱን ሙሉ ስምና አድራሻ በመፃፍ ማህተም በማድረግ በተጠቀለለ አንድ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ዩኒቨርሲቲው ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡- የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓል ቀናት ከሆነ ጨረታው በቀጣዩ የሥራ ቀን ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 058-7-71-66-91 ደብረ ማርቆስ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ
