Tender Detail

Tender Details

  • Company በአብክመ ደቡብ ወሎ ዞን ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር መምሪያ የወረኢሉ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት
  • Address , Phone: 00 00 00 00
  • Website
  • Deadline06 Nov 2024, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Others

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የወረኢሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ውስጥ ላሉ ሴ/መ/ቤቶች ለ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የቢሮ መገልገያ እቃዎችን እና የተሽከርካሪ መለዋወጫ እቃዎች በመደበኛ እና የስፖርት ትጥቅ በስፖርት ምከር ቤት በጀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በሎት መግዛት ይፈልጋል፡፡

በአብክመ ደቡብ ወሎ ዞን ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር መምሪያ የወረኢሉ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት


የብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የወረኢሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ውስጥ ላሉ ሴ/መ/ቤቶች ለ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የቢሮ መገልገያ እቃዎችን እና የተሽከርካሪ መለዋወጫ እቃዎች በመደበኛ እና የስፖርት ትጥቅ በስፖርት ምከር ቤት በጀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በሎት መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም

ሎት 1. የስፖርት ትጥቅ

ሎት 2. የጽህፈት መሳሪያዎች

ሎት 3. የጽዳት እቃዎች

ሎት 4. ቋሚ አላቂ የቢሮ እቃዎች

ሎት 5. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች

ሎት 6. ክሎሪን

ሎት 7. የመኪና መለዋወጫ እቃዎች

ሎት 8. የተለያዩ የውሃ እቃዎችና የግንባታ እቃዎች

ከላይ የተዘረዘሩትን እቃዎች ለማቅረብ በዘርፉ የተሰማራችሁ አቅራቢዎች

  1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ነምበር እና የግዥ መጠን ከ200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል፤
  2. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1/አንድ ላይ የተጠቀሱትን መረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  3. የሚገዛውን እቃ ዝርዝር መግለጫ/ ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፤
  4. ተጫራቾች እያንዳንዱን ሰነድ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከወረኢሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት መውሰድ ይቻላል፣
  5. የጨረታ ሰነድ ጸንቶ የመቆያ ጊዜው ይህ ጨረታ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር ለ40/ አርባ ተከታታይ ቀናት ብቻ ይሆናል፣
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ መ/ቤታችን በወሰነው የጨረታ ዋስትና ማለትም ሎት 1. ላለው ስፖርት ትጥቅ 16,000፣ ብር ሎት 2. ላይ ላለው ጽ/መሳሪያ 67,000 ብር፣ ሎት 3 ላይ ላለው ጽዳት ዕቃ 9,000 ብር፣ ሎት 4 ላይ ላለው ቋሚ አላቂ የቢሮ ዕቃ 7,000 ብር፣ ሎት 5 ላይ ላለው የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች 65,000 ብር፣ ሎት 6 ላይ ያለው ክሎሪን 6,000 ብር ሎት 7 ላይ ላለው የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች ለእያንዳንዱ መኪና 8,000 ብር በተናጠል እና ሎት 8 ላይ ላለው የውሃ ግንባታ እቃዎች 10,000 ብር በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በባንከ በተረጋገጠ ሲፒአ/በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፤ የሚያስይዙትም የዋስትና አይነት ቢያንስ ለ90 ቀናት ጸንቶ መቆየት አለበት፡፡
  7. የጨረታ አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከመ/ቤታችን ጋር የውል ስምምነት ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. በጨረታ ሰነዱ ላይ ዋጋ ያልተሞላበት ከፍት ቦታ ካለ ከጨረታ ውድቅ ይሆናል፤
  9. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለው እና ፓራፍ ካላደረጉ ብሎም የበዛ ስርዝ ድልዝ ካለው ከጨረታው ውድቅ ይሆናሉ፡፡
  10. ተጫራቾች በጨረታው ሰዓት በአካል የማይገኙ ከሆነ በራሳቸው ፈቃድ ጨረታው የሚከፈትበትን ሰዓት የጨረታውን መክፈት የማያስተጓጉል ከመሆኑ በተጨማሪ በጨረታው ሂደት በተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡
  11. ተጫራቾች የጨረታ ሀሳባቸውን በጨረታ ሰነዱ ላይ በመሙላት የድርጅቱን ማህተም በየመጫረቻ ሰነዳቸው ላይ በመጠቀም ዋና እና ኮፒውን በማያያዝ በጥንቃቄ በ2 ፖስታ በማሸግ በወረዳው ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቁጥር 2 በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት በማስገባት ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ድረስ በአየር ላይ ቆይቶ በ16ኛው ቀን ከጧቱ 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጐ በዚሁ ቀን 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በይፋ ይከፈታል፡፡
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ ወረኢሉ ወረዳ ግዥና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት በግንባር በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 033 116 01 99/54 መደወል ይቻላል፡፡

ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች መ/ቤቱ በሚያቀርበው ናሙና መሰረት እቃውን ማቅረብ አለባቸው

 

በአብክመ የደቡብ ወሎ ዞን የወረኢሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

Save Tender