Tender Detail

Tender Details

  • Company የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-8-33-25-01
  • Website
  • Deadline02 Nov 2024, 9:45 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች እና አገልግሎቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ


የጨረታ ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች እና አገልግሎቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ የግዢው መለያ ቁጥር:- BOHEA-PPAD-NCB Recurrent-Budget-2017-1st BID ነው።

ምድብ

የግብአቱ/እቃው/አገልግሎቱ አይነት

የጨረታ ማስከበሪያ

ሎት እንድ

 

የፅህፈት መሳሪያዎች

 

4,000

 

ሎት ሁለት

የፅዳት ዕቃዎች

4,000

 

ሎት ሶስት

የሰራተኞች የደንብ ልብስ

3,000

 

ሎት አራት

የሰራተኞች የደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት

1,500

 

ሎች አምስት

የፕሪንተር እና የፎቶ ኮፒ ማሽን ቶነር

18,000

 

ሎት ስድስት

ጀነሬተር 40 KVA

 

50,000

 

ሎት ሰባት

የሊፍሌት ዲዛይን፣ ህትመት፣ የቪዲዮ ክሊፐ መሥራት

 

8,000

 

ሎት ስምንት

 

የተለያዩ ፈርኒቸሮች እና ቋሚ እቃ የአበባ ማስቀመጫ

 

8,000

 

 

  1. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት የሚያቀርቡ ብሎም በአሁኑ ሰዓት ያሉ መሆን አለባቸው
  2. የቫት ተመዝጋቢ ሆነው ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉና መለያ ቁጥር/ቲን ነበር ያላቸው መሆን አለበት።
  3. ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና በዘርፉ የተሰማሩ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከላይ የተጠቀሰውን ብር በየሎቱ ለየብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. የጨረታ አሸናፊዎች አሸናፊነታቸው ከተገለፀ በኋላ ያሸነፉበትን ዕቃ ወይም አገልግሎተ 10% የውል ማስረከቢያ ሲ ፒ ዮ/ቦንድ ማስያዝ አለባቸው::
  6. ተጫራቾች ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት በየሎቱ ብር 100 በየሎቱ በመክፈል ከመንግስት ግዢ ዳይሬከቶሬት እስከ 10ኛው የስራ ቀን ድረስ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ እስከ 11ኛው የስራ ቀን 3፡45 ድረስ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ዋጋ ሞልቶ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተምና ፊርማ አድርጎ ያላቀረበ ተጫራች ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  9. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የመጫረቻ ሰነድ ፋይናንስ ዋና እና አንድ ኮፒ እንዲሁም ቴክኒካል ዋና እና አንድ ኮፒ ለየብቻ በማድረግ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
  10. ቢሮው በጨረታ ሰነዱ ከተገለጸው የዕቃ /የአገልግሎት ፍላጎት መጠን ጨረታ ሰነዱ ላይ ከውል በፊት 20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
  11. ጨረታው ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ 60 ቀናት ነው፡፡ አንድ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  12. ጨረታው የሚዘጋበት ቀን የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣ ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን ጠዋት 3፡45 ታሽጎ በዕለቱ 4፡15 በመ/ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ይሆናል፡፡
  13. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው

 

አድራሻ፡- አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 01 ማህበራዊ ዋስትና አዲሱ ህንፃ ማህበራዊ ዋስትና የንግድ ማእከል ህንፃ 7ኛ ፎቅ/ፒያሳ ኤንሪኮ ኬክ ቤት አካባቢ) የመንግስት ግዢ ዳይሬክቶሬት

ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር፡- 011-8-33-25-01

 

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ

Save Tender