Tender Detail

Tender Details

  • Company የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የቃሊቲ 2ኛ ደረጀ ት/ቤት
  • Address አዲስ አበባ ፤ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ከቃሊቲ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አለፍ ብሎ ቸራሲያ ሳይደርስ በስተግራ በኩል 150 ሜትር ያህል ገባ ብሎ የሚገኘው የቃሊቲ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት, Phone: 011-4626451
  • Website
  • Deadline01 Nov 2024, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Materials

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የቃሊቲ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የ2017 ዓ.ም የሚከተሉትን የተለያዩ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ ቁጥር 01/2017 አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የቃሊቲ 2ኛ ደረጀ ት/ቤት


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የቃሊቲ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የ2017 ዓ.ም የሚከተሉትን የተለያዩ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ ቁጥር 01/2017 አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ የሠራተኞች የደንብ ልብስ፣ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ የህትመት እቃዎች፣ የህክምና ዕቃዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ አላቂ የትምህርት ዕቃዎች ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፣ የላብራቶሪ እቃዎች እና ልዩ ልዩ ግብአቶች ናቸው:: በዚህ ጨረታ ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባችኋል፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  3. በአቅራቢነት ለመመዝገባቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  4. የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  5. የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር ተመዝጋቢ የሆኑና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  • ተጫራቾች የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር) በመክፈል ቢሮ ቁ.3 (ፋይናንስ ቢሮ) የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  • ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ጨረታ ከመክፈቻው ቀን በፊት ኦርጅናልና ደረጃውን የጠበቁ ናሙናዎች ለት/ቤቱ ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (BID BOND) በየሎቱ የተጠቀሰውን ብር መጠን ሲፒኦ በማሰራት ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

    ሎት 1 የደንብ ልብስ ፡-                                             21,170.00

    ሎት 2 አላቂ የቢሮ ዕቃ ፡-                                         16,069.00

    ሎት 3 የህትመት ዕቃ :-                                            1,700

    ሎት 4 የህክምና ዕቃ ፡-                                             1,600.00

    ሎት 5 አላቂ የትምህርት ዕቃ ፡-                                 26,140.00

    ሎት 6 የፅዳት ዕቃዎች ፡-                                          23,630.00

    ሎት 7 ልዩ ልዩ ዕቃዎች ፡-                                        7,909.00

    ሎት 8 የምርምር ዕቃዎች ፡-                                      1,200

    ሎት 9 ቋሚ ዕቃዎች ፡-                                             32,857.00

    ሎት 10 የላብራቶሪ እቃዎች ፡-                                 1,600

  1. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ በግልፅ ቫትን ጭምሮ ያለውን ዋጋ ድምሩን አካቶ ሙሉ በሙሉ በመሙላት በመጨረሻ ቦታ ላይ ፊርማና የድርጂታቸውን ማህተም በማሳረፍ ኦርጅናልና ኮፒ ሰነድ ለያይቶ በሰም በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ዘወትር በስራ ሠዓት ከ2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁ.3 በመቅረብ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡
  2. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኘበት በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ የተጫራቾች ወይም የህጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት የጨረታውን መክፈት አያስተጓጉልም፡፡
  3. የጨረታ አሸናፊዎቹ ተለይተው ከተገለፁበት ቀነ ገደብ ቀጥሎ ባለው ተከታታይ 7 የስራ ቀናት ውስጥ አሸናፊዎች የውል ማስከበሪያ 10% በማስያዝ ውል መፈፀም አለባቸው፡፡ ላላሸነፉ ተጫራቾች ደግሞ ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  4. አሸናፊዎቹ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው (በተጫራቹ) ትራንስፖርት ቃሊቲ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
  5. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡

አድራሻ፡- አዲስ አበባ ፤ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ከቃሊቲ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አለፍ ብሎ ቸራሲያ ሳይደርስ በስተግራ በኩል 150 ሜትር ያህል ገባ ብሎ የሚገኘው የቃሊቲ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-4626451/ 011-4626324

 

በአዲስ  አበባ  ከተማ  አስተዳደር  በአቃቂ  ቃሊቲ  ክፍለ  ከተማ  የቃሊቲ  2ኛ  ደረጀ  ት/ቤት

Save Tender