Tender Detail

Tender Details

  • Company በወላይታ ዞን ዳሞት ፑላሳ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት
  • Address ወላይታ ፡ ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0465599446
  • Website
  • Deadline21 Oct 2024, 3:59 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Office Machines And Computers

በደቡብ ኢትዯጵያ ክ/መ በወላይታ ዞን የዳሞት ፑላሳ ወረዳ ፋ/ፅ/ቤት በ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት ለወረዳው ሴክተር መ/ቤቶች የዓመታዊ አላቂ የፅ/መሳሪያ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ።

በወላይታ ዞን ዳሞት ፑላሳ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ኢትዯጵያ ክ/መ በወላይታ ዞን የዳሞት ፑላሳ ወረዳ ፋ/ፅ/ቤት በ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት ለወረዳው ሴክተር መ/ቤቶች የዓመታዊ አላቂ የፅ/መሳሪያ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ።

ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ የንግድ ስራ ድርጅቶች ፡-

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ስራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል
  2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
  3. የቫትና የቲን ተመዝጋቢ የሆነ፤
  4. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል ።
  5. አሸናፊ የሆነ ተጫራች የዓመታዊ አላቂ የፅ/መሳሪያ እስከ አጫራች መ/ቤት ድረስ አምጥቶ ለማስረከብ ፈቃደኛ መሆን የሚችል፤
  6. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከዳሞት ፑላሳ ወረዳ ፋ/ፅ/ቤት ቢሮ ቁጥር 04 የማይመለስ 200/ሁለት መቶ ብር በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፤
  7. የጨረታው አሸናፊ ከሆኑ የውል ማስከበሪያ 10% ቢድ ቦንድ/CPO/ ማስያዝ የሚችሉ፤
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ኦርጅናልና የኦርጅናሉን አንድ ፎቶ ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ ሙሉ አድራሻቸውንና የድርጅቱን ስም በመጥቀስ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ መክተት ይኖርባቸዋል ፤
  9. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 (አስራ አምስት) በተከታታይ ቀናት ቀጥሎ በሚውለው በ16ኛው የስራ ቀን 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 8፡30 በዳ/ፑ/ወ/ፋ/ፅ/ቤት ቢሮ ቁጥር 04 ይከፈታል፤
  10. ተጫራቾች በሚያቀርቡት በነጠላ ዋጋ ላይ የማይነበቡና ስርዝ ድልዝ ያለው መሆን የለበትም ።
  11. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ CPO 30,000/ሰላሳ ሺህ ብር/ በማንኛውም ባንክ የተመሰከረላቸውን CPO ማስያዝ የሚችሉ ።

ማሳሰቢያ ፡- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ።

ተጫራቾች ለአጫራች መ/ቤት አሸናፊ ከሆኑ በኃላ የዕቃዎች ናሙና ለማሳየት ፍቃደኛ መሆን የሚችሉ ።

ለበለጠ መረጃ በስ.ቁ 0465599446 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ ።

በደቡብ ኢትዯጵያ ክ/መ በወላይታ ዞን የዳሞት

ፑላሳ ወረዳ ፋ/ፅ/ቤት

Save Tender

ቦሌ ማተሚያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ሎት1.የተለያዩ የህትመት ወረቀቶች፣ የተለያዩ ለህትመት የሚሆኑ ቀለሞች፣ ፎቶፎሊመር ፕሌት እና ኒሜራቶር በጨረታ አወዳድሮ መግ...

READ MORE
ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃ.የተ.የግ.ማህበር የኮምፒውተርና ተዛማች እቃዎች ግዥ

READ MORE
የኦሮሚያ መሬት ቢሮ ቁጥር NCB/06/2019 ለመስሪያ ቤቱ የሚያገለግል ታብሌቶችን ከህጋዊ ድርጅቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::

READ MORE