ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
መክሊት ማይክሮፋይናንስ ኢንስቲትዩሽን ኢ.ማ.
መክሊት ማይክሮፋይናንስ ኢንስቲትዩሽን ኢ.ማ. በመቂ ከተማ የሚገኘውን ቅ/ጽ/ቤት የአጥር ዕድሳት፣ የቢሮእድሳትና የመጋዘን ግንባታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማስራት ይፈልጋል፡፡
በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች አሞልትው መቅረብ ያለባቸው መስፈርቶችና ግዲታዎች
1. በግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት መመዝገባቸው የሚያረጋግጥ የምዝገባ ስርተፍኬት ማቅረብየሚችል!
2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስከር ወረቀት' የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ በሚወዳደሩበት ንግድ ዘርፍ የታደስሕጋዊ ንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ
3. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የጨረታ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከታተመበት ቀን አንስቶ በተከታታይእስከ 15ኛው ቀን ድረስ ዘውትር በሥራ ሰዓት በተቋሙ ዋና መ/ቤት ወይም ግንባታው በሚከናወንበት መቂ ቅርንጫፍዘወትር በሥራ ሰዓት ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች ከጨረታ ግምግማ በኋላ ለተሸናፊዎች የሚመለስ የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ ባቀረቡት ጠቅላላ ዋጋላይ በማስላት 2% በባንክ የተመሠከረበት በመክሊት ማይክሮፋይናንስ ኢንስቲትዩሽን አ.ማ. የተሠራውን ሲፒኦ ከጨረታማቅረቢያ ሰነድ ጋር አያይዘው በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. አሸናፊ የሆነ ተጫራች የውል ማስከበሪያ ዋስትና አሸናፊነቱ ከተረጋገጠበት ከተገለፀበት ቀን አንስቶ ባለት ሦስትተከታታይ ቀናት ውስጥ በአሸነፉበት ዋጋ መጠን ተሰልቶ 5% በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ በባንክ በተመሠክረ ሲፒኦማስያዝ አለበት፡፡ ለማስያዝ ፈቃደኛ ካልሆነ ለጨረታው ዋስትና ያስያዘው ብር በሙለ በተቋሙ ውርስ ይደረጋል፡፡
6. አንድ ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብና አሸናፊነቱ ከተገለፀ በኋላ አላቀርብም ማለትየጨረታ ዋስትናውን ያስቀጣል።
7. ተጫራቾች በተቆሙ በተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ ላይ በቻ ዋጋ እንዲያቀርብ ይገደዳሉ ከተቆሙ ቅጽ ውጪ የሚቀርብመወዳደሪያ ከጨረታው ያሰርዛል፡፡ ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ መወዳደሪያ ሰነድ ዋናውንና ሌሎች ህጋዊማስረጃዎች ፎቶኮፒውን በታሸገ ፖስታ የድርጅቱን ሕጋዊ ማህተምና ፈርማ በማድረግ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀውጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
8. የጨረታ ፖስታ በጨረታ ሣጥን የሚገባው የጨረታ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ይፋ ከሆነበት ቀን አንስቶ ቅዳሜናእሁድ ጨምሮ በተከታታይ እስከ 15ኛው ቀን ከሰዓት በኅላ 10:00 ሰዓት ድረስ ገቢ ሆኖ በ10፡30 ላይ የጨረታ ሳጥንይዘጋል፡፡ በማግስቱ ጧት 4:00 ሰዓት ጨረታ ሣጥን ፈቃደኛ የሆኑ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዩቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል። አስራ አምስተኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም ሕጋዊ በዓል ቀናት ከዋለ በሚቀጥለው ሥራ ቀንበተመሣሣይ ሰዓትና ቦታ ይከፈታል፡፡
9. አንድ ተጫራች የሚያሠራው ሲፒኦ በሕጋዊ ባለመብት ወይም ድርጅት ስም የተሠራ መሆን
10. አንድ ተጫራች በጨረታ ሰነድ ውስጥ የተዘረዘሩ ሥራዎችን በሙስም ሆነ በከፊል መጫረት
11. የጨረታ ሰነድ ስርዝ ድልዝ ካለው ወይም ግልፅ ሆኖ ካልታየ ተቀባይነት አይኖረውም።
12. ተቋሙ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ
► በተቋሙ ዋና መ/ቤት ሲኤምሲ አካባቢ በሚገኘው አዲስ አፍሪካ አለም አቀፍ ኮንቬንሽንና ኤግዚቢሽን ማዕክል 1ኛፎቅ ቢሮ ቁጥር 106 በአካል በመቅረብ፣
► በተቋሙ መቂ ቅርንጫፍ መቂ ከተማ መክሊት ማይክሮፋይናንስ በአካል በመቅረብ፣
► በስልክ ቁጥር 09-29-08-06-63 ወይም 09-22-29-35-91 በመደወል፣ መረጃ ማገኘት ይቻላል፡፡
መክሊት ማይክሮፋይናንስ አ.ማ. እምቅ አቅምምን ወደ ትሩፋት የሚለውጡበት ተቋም
