ናሽናል ሲሚንቶ አ.ማ. ለድርጅቱ ጥበቃ ሠራተኞች ዩኒፎርም ሙሉ ልብስ ሸሚዝና ሱሪ (ሸሚዙ እጅጌ ሙሉ) ካኪ (ኮተን) ቀለም ቁጥር 270 ፣ የሸሚዙ የግራ ደረት ኪሱ ላይ የድርጅቱ አርማ በጥልፍ መልክ (Embroidery type) ያለው ፣ ጫማ (Shoes for security) ቁጥር 270 በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
ናሽናል ሲሚንቶ አ.ማ ለድርጅቱ ጥበቃ ሠራተኞች ከዚህ በታች በተገለጸው የአልባሳት አይነት በዘርፉ ላይ ከተሰማሩ ተጫራቾች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- ዩኒፎርም ሙሉ ልብስ ሸሚዝና ሱሪ (ሸሚዙ እጅጌ ሙሉ) ካኪ (ኮተን) ቀለም ቁጥር 270
- የሸሚዙ የግራ ደረት ኪሱ ላይ የድርጅቱ አርማ በጥልፍ መልክ (Embroidery type) ያለው
- ጫማ (Shoes for security) ቁጥር 270
በመሆኑም ተጫራቾች:
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና ቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ከላይ የተገለጸውን አልባሳት አይነቶች የአንዱን ዋጋ በግልጽ በማስቀመጥ እንዲሁም የአልባሳቶቹን ስፌት ናሙና (sample) ሳር ቤት ግደይ ገ/ህይወት ህንጻ 3ኛ ፎቅ አ.አ. ስልክ፡ 251-114-421928/09-30-30-41-10 ግዢ ክፍል እና ድሬዳዋ ናሽናል ሲሚንቶ ኢማ ስልክ ቁጥር 0935-98-50-83/0946-43-93-94 ግዢ ክፍል በታሸገ ፖስታ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ላሉት 3 ወራት ህጋዊ ሆኖ የሚቆይ የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ. 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ) ብር ማስያዝ አለባቸው፡፡
- የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ባሉት ቀናት የሚቆይ ሆኖ ማለትም ነሀሴ 14/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ጨረታው ተዘግቶ ነሀሴ 18/2016 ዓ.ም ድሬዳዋ በሚገኘው ናሽናል ሲሚንቶ አ.ማ ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኋላ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
ማሳሰቢያ፡-
ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ተከፍቶ ውሳኔ ይሰጥበታል፡፡ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡
ናሽናል ሲሚንቶ አ.ማ.
