ናሽናል ሲሚንቶ አ.ማ. UPS 15KVA ከአቅራቢዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
National Cement S.C (ናሽናል ሲሚንቶ አ.ማ.)
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ናሽናል ሲሚንቶ አ.ማ. UPS 15KVA ከአቅራቢዎች አወዳድሮ ለመግዛት ጨረታ ያወጣ ሲሆን
ተጫራቾች
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉና ቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ላሉት 3 ወራት ህጋዊ ሆኖ የሚቆይ የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ. 50,000.00 (ሀምሳ ሺህ) ብር ማስያዝ አለባቸው፡፡
- የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ባሉት ቀናት እስከ ሐምሌ 24/2016 ዓ.ም ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን ሐምሌ 24/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ጨረታው ተዘግቶ ሐምሌ 29/2016 ዓ.ም ድሬዳዋ በሚገኘው ናሽናል ሲሚንቶ ኢማ ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ከላይ በተገለጸው መስፈርት መሰረት የአንዱን UPS 15KVA ዋጋ በግልጽ በማስቀመጥ ሳር ቤት ግደይ ገ/ህይወት ህንጻ 3ኛ ፎቅ አ.አ. ስልክ፡ 25 1114 42 19 28/0960-36-71-36 ግዢ ክፍል እና ድሬዳዋ ናሽናል ሲሚንቶ ኢማ ስልክ ቁጥር 0935- 98-50-53/0946-43 93 94 ግዢ ክፍል በ ፖስታ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኋላ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
ማሳሰቢያ፡-
- ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ተከፍቶ ውሳኔ ይሰጥበታል፡፡ መ/ቤቱም የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው።
ናሽናል ሲሚንቶ አ/ማ
