በታክስ ዕዳ የተያዙት ተሸከርካሪዎች ለመሽጥ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ የጨርታ ቁጥር 7/2016
Ministry of Revenues (የገቢዎች ሚኒስቴር)
የሚኒስቴር መ/ቤቱ ግብር ከፋዮች የሚጠበቅባቸውን የታክስ ዕዳ በታክስ ህጉ በተፈቀደው የጌዜ ገደብ ባለመክፈላቸው ምክንያት በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀፅ 41 በተሠጠው ስልጣን መሠረት ኤቪ አንዱስትሪስ ስቴል ኃ/የተ/የግ/ማህበር፣ ቲ አይ ቢ ኬተሪንግ ሰርቨስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር እንዲሁም አክሰፎርድ አማልጌትድ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተያዙ 3 ተሸከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሽጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም፡
1 በግልፅ ጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ማንነቱን የሚገልጽ የነዋሪነት መታወቂያ (ፓስፖርት) ኮፒ ከጨረታ ስነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ በማሸግ ለግልፅ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል
2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ የግልፅ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሰራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2:00-6፡00 ሰዓት ህንፃ "ለ" 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 ከግዥና ፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬከቶሬት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመከፈል የጨረታ ሰነዱን ህንፃ "ሆ" 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 202 ከታክስ ዕዳ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ መውሰድ ይኖርባቸዋል፡
3. በግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ንብረቶች የሰጡትን ዋጋ /o ኛውን ብቻ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) በገቢዎች ሚኒስቴር ስም (Minstry of Revenue) በባንክ አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት ሰነድ ገዝተው መጫረት ይችላሉ፡፡
|
ተ.ቁ |
የመ/ቤቱ ስም |
ለጨረታ የቀረበው የንብረት ዓይነት |
የተሽከሪዎች መመልከቻ ቀን |
የጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
|
ገቢዎች ሚኒስቴር |
ተሽከርካሪዎች |
ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ቀናት |
ማስታወቂያ በጋዜጣ ወጥቶ ቀጥሎ ባለው 16ኛ ቀን 3፡45 ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡00 ሰዓት የከፈታል |
5. የጨረታ መከፈቻ ቦታ:-
6 መገናኛ በሚገኘው በሚኒስቴር መ/ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ውይም በታዛቢያቾች ይክፈታል
7. የግልፅ ጨረታው መከፈቻና መዝጊያ 16ኛው ቀን የመ/ቤቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን የግልፅ ጨረታ መክፈቻና መዝጊያ ቀን ይሆናል፡፡
8. ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያስያዙት (CPO) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር እንደ አስፈላጊነቱ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሽናፊ ተጫራቾች ደግሞ የግልፅ ጨረታ ኮሚቴው መረጃው አጣርቶ እንደጨረሰ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
9. የተሽከርካሪ ጨረታ ለሚያሸንፉ ተጫራቾች ከስመ ንብረት ዝውውር ጋር ተያያት 10 ያላቸውን ወጪዎች (የቦሎና ሌሎች ተጓዳኝ ወጪዎች) ሻጭን አይመለከትም::
10. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ ያሸነፉብትን ጠቅላላ ዋጋ መ/ቤቱ በሚሠጠው አድራሻ ገቢ በማድረግ ያሸነፋበትን ሀብት/ንብረት መረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
11. ከላይ በተ/ቁ 9 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ከፍያውን ገቢ በማድረግ ንብረታቸውን ያልተረከቡ ተጫራቾች የግልፅ ጨረታው ተሠርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በርPO ያስያዙት የዋስትና ገንዘብ ለሚኒስቴር መ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ንብረቱ እንዳልተሸጠ ተቆጥሮ በቀጣይ በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
12. ሚኒስቴር መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ የግልፅ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ መረጃ፦በስልክ ቁጥር 011-617-84-90 (2044) (2045) (208) የውስጥ መስመር (EXT) 2044 ደውለው መጠየቅ ወይም የተቋሙን ዌብሳይት www.MOR.Gov.et መመልከት ይቻላል፡፡
የኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር
