በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልል መንግስት በጌዴኦ ዞን የጨለለቅቱ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በ2015 በጀት አመት በጨለለቅቱ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል G+1 ህንጻ ግንባታ ለመገንባት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2015
በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልል መንግስት በጌዴኦ ዞን የጨለለቅቱ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በ2015 በጀት አመት በጨለለቅቱ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል G+1 ህንጻ ግንባታ ለመገንባት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾችን እንዲወዳደሩ ደፈልጋል።
- በዘመኑ የታደሰ ንግድ ሥራ ፍቃድ ያላቸዉ VAT/TOT/TIN የተመዘገቡበት የምስክር ወረቀት ከሚመለከታቸው የመንግስት አካል ማቅረብ የሚችል።
- ሕጋዊ የግንባታ ሥራ ፍቃድ GC-6/BC-5 እና ከዚያ በላይ ያላቸው።
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 25,500 /ሃያ አምስት ሺህ አምስት መቶ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ የሚችል።
- አሸናፊ ተጫራች ውል ሲፈራረሙ የመልካም ሥራ አፈጻጻም ዋስትና ያስገባውን ዋጋ 10% ማስገባት ይኖርበታል።
- ተወዳዳሪዎች እያንዳንዱን ዋጋ ከፋይናንስ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ30 ቀናት የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ/ ብር ብቻ በመክፈል በፍርድ ቤቱ ቢሮ ቀርቦ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ Technical and Financial ዶክመንት አንድ አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ሁለት copy በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማህተም በማረጋገጥ እስከ 30 ቀን ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ በማስገባት ይኖርባችኋል። በ31ኛው ቀን 3:30 ሰዓት ተዘግቶ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል። ዕለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል። ለተሸነፉት ተጫራቾች ወዲያውኑ ያስያዙት ሲፒኦ/CPO/ ይመለስላቸዋል።
- የቀረበ ዋጋ VAT መጨመሩንና አለመጨመሩን መግለጽ አለባቸው።
- ፍርድ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ: በጌዴኦ ዞን የጨለለቅቱ ከተማ አስተዳደር ከተማ
ስልክ ቁጥር፡- 0912-45-57-10/0926-15-39-32
በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልል መንግስት
በጌዲኦ ዞን ጨለለቅቱ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት
