የአብክመ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት የበግ እና የከብት ስጋ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል
በድጋሜ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የአብክመ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት በ2015 ለመጀመሪያዉ ግማሽ በጀት ዓመት ከሐምሌ 01/2014 ዓም እስከ ታህሳስ 30/2015 ዓም ድረስ በግቢው ውስጥ ለሚሰጡ ስልጠናዎች ለሠልጣኞች አገልግሎት የሚውሉ የበግ እና የከብት ስጋ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል::
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- . የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ጀርባዉ ላይ ከዋናዉ ጋር ተገናዝቧል በማለት ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50/ሃምሳ ብር /በመክፈል በአመራር ኢንስቲትዩቱ ግቢ ቢሮ ቁጥር 19 መግዛት ይችላሉ፡፡
- . የሚገዙ የዕቃዎችን/አገልግሎቶችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በመግለፅ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ከሐምሌ 04/2014 ዓ/ም ጀምሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በኢንስቲትዩቱ የግዥ እና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 19 ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ብር 85,000/ሰማኒያ አምስት ሽህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በአካዳሚው ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን አንድ ወጥ በሆነ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ በኢንስቲትዩቱ ግዥ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ወይም ቢሮ ቁጥር 19 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሐምሌ 04/2014 እስከ ሐምሌ 19/2014 ዓ.ም 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
- ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ሐምሌ 19/2014 ዓ.ም 4፡00 ታሽጎ 4:30 ይከፈታል፡፡
- . የመክፈቻው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ስዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ኢንስቲትዩቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- . በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት የለዉም፣
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 19 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም ስልክ ቁጥር 0582262360 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአብክመ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት
