በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 የእህል ንግድ 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ማህበር የመኖሪያ መንደሩን አጥርና የጥበቃ ቤቶችን የግንባታ እና የባለሙያ እጅ ስራ ዋጋ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ቦ/ክ/ከ/እ/ን/ኮ/መ/ቤ/ማ-001/2014
በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 የእህል ንግድ 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ማህበር የመኖሪያ መንደሩን አጥርና የጥበቃ ቤቶችን የግንባታ እና የባለሙያ እጅ ስራ ዋጋ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
መግለጫ |
ደረጃ |
የጨረታ ማስከበሪያ |
የመዝጊያ ቀን እና ሰዓት |
የመክፈቻ ቀን እና ሰዓት |
|
ሎት-1 |
የአጥርና የጥበቃ ቤት ግንባታ ስራ |
07 |
30,000 |
ሐምሌ 19 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 4:00 |
ሐምሌ 19 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 4:30 |
|
ሎት-2 |
የአጥርና የጥበቃ ቤት ግንባታ የባለሙያ እጅ ስራ |
07
|
15,000 |
- ተጫራቾች በህንጻ ግንባታ ወይም በአጠቃላይ ግንባታ ደረጃ 07 እና ከዛ በላይ የሆነ የግንባታ ፈቃድ ያላቸውና የታደሰ ንግድ ስራ ፍቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማያያዝ አለባቸው።
- በእያንዳንዱ ሎት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 ብር በመክፈል በቦሌ ክፍለ ከተማ እህል ንግድ የጋራ መኖሪያ ቤት ባለቤቶች ማኅበር ብሎክ 06 አንደኛ ፎቅ በሚገኘው የማህበሩ ቢሮ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሐምሌ 18/2014 ዓ.ም ድረስ ማግኘት ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1 ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺ ብር) እና ለሎት 2 15000 ብር ቦሌ ክፍል ከተማ የእህል ንግድ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ማኅበር ስም በባንክ በተረጋገጠ ጋራንቲ ወይም ሲፒኦ ለእያንዳንዱ ሎት ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ሰነድ በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ ጨረታ ቁጥር ቦ/ክ/ከ/እ/ን/ኮ/መ/ቤ/ማ-001/2014 የሚል ምልከት በማድረግ እስከ ሐምሌ 19 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ከላይ በተጠቀሱት አድራሻ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሐምሌ 19 ቀን 2014 ዓ.ም ከላይ በተጠቀሱት አድራሻዎች በ4፡30 ይከፈታል።
- ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ካስፈለገ ዘወትር በስራ ሰዓት በስልክ ቁጥር +251 11 863 98 62 በመደወል ወይም ከላይ በተጠቀሰው የማህበሩ ቢሮ በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ።
- ማህበሩ የተሻለ ዘዴ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የቦሌ ክፍለ ከተማ የእህል ንግድ የጋራ መኖሪያ ቤት ባለቤቶች ማኅበር
