ኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራንስ አ.ማ. የካሣ ክፍያ ፈጽሞ የተረከባቸውን ተሽከርካሪዎችንና ልዩ ልዩ የተሽከርካሪ አካላት ቅሪቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::
Ethio Life and General Insurance S.C (ኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራንስ አ.ማ)
የጨረታ ማስታወቂያ
ኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራንስ አ.ማ. የካሣ ክፍያ ፈጽሞ የተረከባቸውን ተሽከርካሪዎችንና ልዩ ልዩ የተሽከርካሪ አካላት ቅሪቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::
- ተሽከርካሪዎችንና ልዩ ልዩ የተሽከርካሪ አካላት ቅሪቶችን ለመግዛት በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ሁሉ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ከራውን ሆቴል ጀርባ ከኢትዮጵያ መድን ድርጅት ተሽከርካሪ ማቆያ ወረድ ብሎ በሚገኘው የኩባንያው ተሽከርካሪ ማቆያ (Recovery Site) ከህዳር 7 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ ህዳር 18 ቀን 2019 ዓ.ም ባሉት የሥራ ቀናት በመምጣት ማየት ይቻላል::
- ተጫራቾች ተሽከርካሪዎችንና ልዩ ልዩ የተሽከርካሪ አካላትን ቅሪቶችን የሚገዙበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ከህዳር 7 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ ህዳር 18 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ባሉት የሥራ ቀናት ከቀኑ 11:00 ሰዓት ድረስ ከመስቀል ፍላወር ወደ ደንበል በሚወስደው መንገድ ቶሊፐ ሆቴል ፊት ለፊት 4ኛ ፎቅ በሚገኘው የኩባንያው ዋና መ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይቻላል::
- ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 10% በባንክ በተረጋገጠ ማዘዣ ለጨረታ ማስከበሪያ(CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል::
- የጨረታው አሸናፊዎች የተሽከርካሪውን ዋጋ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ የጨረታ ውጤት በተገለፀ በ10 ቀናት ውስጥ ከፍለው በ10 ቀናት ውስጥ ንብረቱን ከግቢው ማንሳት ይኖርባቸዋል::
- የጨረታ ዋጋ ተንተርሶ ሌላ ዋጋ መስጠት አይቻልም:: የጨረታ ዋጋ አባዝቶ ማቅረብ አይቻልም::
- ተሽከርካሪው በጨረታ እስከ ተሸጠበት ጊዜ ድረስ የሚፈለግ ግብርና ታክስ ቢኖር ጨረታውን አሸንፈው የሚገዙ አይጠየቁበትም:: ተሽከርካሪው ከተሸጠ በኋላ የሚፈለግ ግብር ታክስና እንዲሁም ተሽከርካሪው ላይ የሚፈለግ የቦሎ ክፍያና ተያያዥ ቢኖር የገዥው ኃላፊነት ይሆናል::
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስን የሚያጠቃልል መሆኑን በግልፅ ሁኔታ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል ::ነገር ግን ባላቀረቡት ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ ተጨምሮ የሚታሰብ ይሆናል::
- አሸናፊ ተጫራቾች ተሽከርካሪውን በራሳቸው ወጪ አስነስተው ይወስዳሉ::
- ተጫራቾች ስለተሽከርካሪዎቹ መንገድ ትራንስፖርት በሰጠው ውሳኔና በጨረታው ሰነድ ላይ በተገለፀው መሠረት ከግምት ውስጥ በማስገባት ዋጋ መስጠት ይኖርባቸዋል::
- ጨረታው ቅዳሜ ህዳር 19 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት በኩባንያው ዋና መ/ቤት ይከፈታል::
ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115549650/0911157195/0911153169 ደውለው መረጃ ማግኘት ይችላሉ::
ኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራንስ አ.ማ
✨ messages.ai_summary
Ethio Life and General Insurance S.C. is selling vehicles and vehicle body salvage taken over after paying insurance claims. Items can be viewed at its recovery site in Akaki Kality. Open bid.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
