የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት ለወልቂጤ ከተማ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የጠጠር መንገድ ጥገና ስራ የሚውል የገረጋንቲ ግብዓት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ያወጣው ማስታወቂያ።
የወልቂጤ ከተማ ፋይናንስ ፅ/ቤት
የገረጋንቲ ግብዓት አቅርቦት ጨረታ ማስታወቂያ
የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት ለ2019 በጀት አመት ለወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ለሚያሰራው ማለትም የጠጠር መንገድ ጥገና ስራ የሚሆን የገረጋንቲ ግብዓት ግዥ ማድረግ ስለሚፈልግ በዘርፉ ከተሰማሩና ህጋዊ ፍቃድ ካላቸው አቅራቢዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በዚህም መሰረት:-
1ኛ/ በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ የስራ ፍቃድ ያላችሁ፤ የዘመኑ የስራ ግብር እና የታክስ ክሊራንስ ከገቢዎች መረጃ ማምጣት የምትችሉ ፣ቲን ነምበር ተመዝጋቢ የሆናችሁና የቫት ሰርተፍኬት ያላችሁ ማህበራት
2ኛ/ በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ በወልቂጤ ከተማ ፋይናንስ ፅ/ቤት ስም ከታወቀ ባንክ የ50,000.00/ ሀምሳ ሺህ ብር/ሲ.ፒ.ኦ. (CPO)ማቅረብ ይጠበቅባችኋል።
3ኛ/ ተጫራቾች በፌደራል መንግስት የግዥ ስርዓት በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና ኢ-ጂፒ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ።
4ኛ/ ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን፤በ22ተኛው ቀን ከቀኑ 8:00 ሰአት ላይ የጨረታው ሳጥን ታሽጎ በዚሁ ቀን በ8:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።
5ኛ/ተወዳዳሪዎች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200(ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ከወልቂጤ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥ ክፍል መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
ማሳሰቢያ
- መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም የጨረታው ኮሚቴ ጨረታው ሊከፍት ይችላል።
- በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ የሌለው ተወዳዳሪ በጨረታው መሳተፍ አይችልም።
- የጨረታው መከፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ቀን ከሆነ ቀጣይ ወዳለው የስራ ቀን ይዘዋወራል።
- ተጫራቾች በመወዳደሪያ ሰነዳቸው በሁሉም ገጽ እና ፖስታ ላይ ስማቸውን ፊርማቸውንና ማህተም ማሳረፍ አለባቸው።
- መ/ቤቱ ከሸጠው ሰነድ ውጪ በሌላ ሰነድ ሞልቶ መወዳደር አይቻልም።
- የመልካም አፈጻጸም ችግር ያለባቸው ድርጅቶች ወይም ማህበራት መወዳደር አይችሉም።
- ተጫራቾች ከዚህ በፊት ስራ ወስደው በጃቸው ያለ ወይም ያላስረከቡ በጨረታው መሳተፍ አይችሉም።
