በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 9 የሚገኘው ልደታ ልማት የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት አላቂ የቢሮና የትምህርት ዕቃዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ ቋሚ እቃዎችና ሕትመት መፅሐፍት በ4 ሎት በግዥ መለያ ቁጥር 02/2019 በግልፅ ጨረታ ለመግዛት ያወጣው ማስታወቂያ።
በልደታ ክ/ከተማ ት/ጽ/ቤት ልደታ ልማት የመጀ/መካ/ደ/ት/ቤት
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥው መለያ ቁጥር 02/2019ዓ.ም
በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 9 አስተዳደር ስር ያለው ልደታ ልማት የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የ2019ዓ.ም በጀት ዓመት የሚያስፈልገውን
- ሎት1. አላቂ የቢሮና የትምህርት ዕቃዎች .......የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 50,000.00
- ሎት 2. የጽዳት እቃዎች.......የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 10,000.00
- ሎት 3. የቋሚ እቃዎች.......የጨረታ ማስከበርያ በብር መጠን 300,000.00
- ሎት4.ሕትመት መፅሐፍት ግዥ.......የጨረታ ማስከበርያ በብር መጠን 5,000.00
ብቃት ያላቸውና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾች አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል። በዚህም መሰረት:-
- በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግስት ግ/ን/አስ/ኤጀንሲ ድረ ገጽ ላይ በአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር የተመዘገቡ የቲንና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች ጨረታውን በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ጨረታቸው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ በተከታታይ 10 የስራ ቀናት ውስጥ የማይመለስስ ብር 300(ሶስት መቶ )በመክፈል በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ልደታ ልማት የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ ።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ10ኛው (አስረኛው) ቀን በ11:00 ሰዓት ታሽጎ በማግስቱ 3:00 ሰአት በልደታ ልማት የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ይከፈታል።
- የመክፈቻው ቀን ቅዳሜ፣ እሁድ ወይም በበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ የስራ ቀን ታሽጎ ይከፈታል። ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት በተወዳደሩባቸው ሎት 1 ሎት 2 ሎት 3 ሎት 4 ናሙና ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን በቀረበው የፍላጎት መግለጫ መሰረት የተሟላ የፍላጎት መግለጫ ማዘጋጀትና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል ።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸው እቃዎች የሞሉት ዋጋ ከቫት ጋር መሆኑን መለየት አለባቸው።
- የዘገየ ጨረታና ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም።
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸው እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈጻሚው መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ(ጥያቄ)
አድራሻ ልደታ ክ/ከተማ በወረዳ 09 ስር የሚገኘው ልደታ ልማት የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
ስልክ ቁጥር:- 0115577520/0115578474
ልደታ ልማት የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
Summary
Lideta Limat Primary and Middle School, Lideta Sub-City Woreda 9, Addis Ababa, buys in four lots by open tender: office and school consumables, cleaning items, fixed items, and printed books. Bidders need a renewed licence, paid tax, PPA supplier registration, TIN and VAT.
