Procurement of Training and Capacity Building (Consultancy Services)
City Government of Addis Ababa Cleansing Management Agency
Tender Information
| Title | Procurement of Training and Capacity Building (Consultancy Services) |
| Description | Procurement of Training and Capacity Building (Consultancy Services) |
| Procuring Entity | City Government of Addis Ababa Cleansing Management Agency |
| Reference No | CMA-NCB-C-0033-2019-PUR |
| Procurement Method | Open |
| Submission Deadline | 2026-11-06 08:30:00 |
| Invitation Date | 2026-10-27 08:30:00 |
| Procurement Type | Shopping |
| Award Type | Item based |
Contact Information
| Physical Address: | Eri Bekentu, Piassa , Addis Ababa, Arada, Addis Ababa, 1415, Ethiopia, Room 10th Floor Addis Ababa, Ethiopia |
| Contact Details: | Tel: +251 112750002 Email: aregawiyemane082@gmail.com |
| Mailing Address: | P.O. Box 00, Postal Code: 00 |
Eligibility Requirements
- •Valid Trade License: Valid Trade License
- •Vat Registration Certificate: Vat Registration Certificate
- •Valid Tax Clearance Certificate: Valid Tax Clearance Certificate
- •Business Organization Registration Certificate: Business Organization Registration Certificate
- •Other Documents: TIN Number
- •Other Documents: የስልጠና አገልግሎት ፕሮፖዛል ለማቅረብ የውድድር ጥሪ ርዕስ፡ በ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ለኤጀንሲው ሠራተኞች በማይንድሴት (Mindset) ዙሪያ ስልጠና ለመስጠት የሙያ ብቃት ላላቸው አሠልጣኞችና ድርጅቶች የቀረበ ጥሪ የጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ በ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ለሠራተኞቹ በማይንድሴት (Mindset) ዙሪያ ስልጠና ለመስጠት በዓመታዊ ዕቅዱ ይዞ ይገኛል። በመሆኑም ኤጀንሲው በማይንድሴት ስልጠና ዘርፍ በቂ የትምህርት ዝግጅት፣ የሙያ ብቃትና ተግባራዊ ልምድ ያላቸውን የግል አማካሪዎች፣ አሠልጣኞች ወይም ድርጅቶች የስልጠና ፕሮፖዛል እንዲያቀርቡ በዚህ ይጋብዛል። 1. የስልጠናው ዓላማ የስልጠናው ዋና ዓላማ ሠራተኞች በማይንድሴት መርሆዎች ላይ የተመሠረተ አዎንታዊ የሥራ አመለካከት እንዲያዳብሩ፣ የመማርና የራስን የማሻሻል ባህልን እንዲያጎለብቱ፣ በተግዳሮቶች ወቅት የመፍትሔ አፈላላጊነትን እንዲያጠናክሩ እና የግልና የቡድን የሥራ አፈጻጸምን እንዲያሻሽሉ ማስቻል ነው። 2. የስልጠናው ወሰን o የማይንድሴት ጽንሰ-ሐሳብና መርሆዎች። o የቋሚ አስተሳሰብ (Fixed Mindset) እና የእድገት አስተሳሰብ (Growth Mindset) ልዩነት። o አዎንታዊ የሥራ አመለካከትና የሥራ ተነሳሽነት ማጎልበት። o የለውጥ አስተዳደርና ከለውጥ ጋር መላመድ። o የቡድን ሥራ፣ ግንኙነትና ተግባቦት። o ችግር ፈቺነት፣ ፈጠራና የውሳኔ አሰጣጥ። o በሥራ ቦታ ተጠያቂነት፣ ቁርጠኝነትና የውጤት ተኮር አሠራር። 3. የአሠልጣኞችና ድርጅቶች መስፈርቶች o በማይንድሴት፣ በሰው ኃይል ልማት፣ በአመራር ወይም ተዛማጅ ዘርፎች የትምህርት ዝግጅትና የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ። o ተመሳሳይ ስልጠናዎችን በመስጠት ያካበቱትን ልምድ በማስረጃ ማቅረብ። o ከሠራተኞች የሥራ ሁኔታና ከኤጀንሲው ዓላማ ጋር የተጣጣመ የስልጠና ሥርዓተ-ትምህርትና የስልጠና ዘዴ ማቅረብ። o የስልጠና ጊዜ ሰሌዳ፣ የሚያስፈልጉ የስልጠና ቁሳቁሶችና የውጤት መለኪያዎችን ማቅረብ። o ዝርዝር የዋጋ ማቅረቢያና የፋይናንስ ፕሮፖዛል ማቅረብ። o ተግባራዊ ልምምዶችን፣ የቡድን ውይይቶችንና የሁኔታ ትንተናዎችን ያካተተ የስልጠና ዘዴ መጠቀም 4. የሚቀርቡ ሰነዶች ፍላጎት ያላቸው ባለሙያዎችና ድርጅቶች የትምህርትና የሙያ ማስረጃዎችን፣ የሥራ ልምድ ማስረጃን፣ የስልጠና ቴክኒካዊ ፕሮፖዛልን፣ የፋይናንስ ፕሮፖዛልንና አስፈላጊ የድርጅት ሕጋዊ ሰነዶችን ማቅረብ ይኖርባቸዋል። 5. የግምገማ መስፈርቶች የሚቀርቡ ፕሮፖዛሎች በቴክኒካዊ ብቃት፣ በሙያ ልምድ፣ በስልጠና ዘዴና በሥራ ዕቅድ ተስማሚነት፣ በሚጠበቀው ውጤት እና በፋይናንስ ፕሮፖዛል መሠረት በኤጀንሲው የግዥ ሥርዓትና በሚመለከተው የግምገማ መስፈርት መሠረት ይገመገማሉ። 6. የማቅረቢያ ቀንና ቦታ o የሰነድ ማቅረቢያ የመጨረሻ ቀን፡ በ EGP system o የማቅረቢያ ቦታ፡ ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ 10ኛ ፉቅ o የመገናኛ ስልክ፡ ---------------------------------------------- o የኢሜይል አድራሻ፡ ------------------------------------ የፋይናንስ ፕሮፖዛል (Financial Proposal) አቀራረብ በሚመለከት የስልጠናው ርዕስ፡ በማይንድሴት (Mindset) ዙሪያ የሠራተኞች አቅም ግንባታ ስልጠና የግዥ ዓይነት፡ የስልጠና አገልግሎት የግዥ ፈጻሚ መ/ቤት፡ የጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ የፕሮፖዛል አቅራቢ፡ [የድርጅት/የባለሙያ ስም] የበጀት ዓመት፡ 2019 ዓ.ም የአቅራቢዎች የፋይናንሻል ፕሮፖዛል ማጠቃለያ ለአቅራቢዎች በሚዘጋጀው የፋይናንሻል ፕሮፖዛል ማቅረቢያ መሠረት፣ የወጪ ዝርዝሮች በግልጽ እና በተቀመጠው መልኩ መቅረብ አለባቸው። #የፕሮፖዛሉ መዋቅር በሰዓት የሚሰላውን የሠልጠና ክፍያ የሚሸፍነውን ክፍል ፣ #እንዲሁም የሠልጠና ማቴሪያል ዝግጅት፣ መመሪያና ማተሚያ ወጪዎች፣ #የሠልጠና አቅርቦትና መሣሪያዎች፣ #የትራንስፖርት ወጪ፣ #የምግብና መጠጥ ወጪ፣ #የቀድሞና ድህረ-ሰልጠና ግምገማ፣ #የሪፖርት ዝግጅትና ማቅረብ **ሁሉም የአንድ ሰዓት ዋጋዎች አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የ15% ታክስን (VAT) ጨምሮ መቅረብ የሚገባቸው ሲሆን፣ በመጨረሻም ጠቅላላ ድምር፣ ተፈጻሚ ከሆነ ታክስ ጋር፣ እና አጠቃላይ የፋይናንሻል ፕሮፖዛል መጠኑን በማካተት መጠናቀቅ አለበት
Bid Security
Amount: 0 ETB
Terms and Conditions
ኤጀንሲው ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡
